bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Exodus 37
Exodus 37
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 36
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 38 →
1
ባጽልኤልም ከግራር እንጨት የቃል ኪዳኑን ታቦት ሠራ፤ ርዝመቱ መቶ ዐሥር ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑ ስፋት ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር፥ ቁመቱም ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር ነበር።
2
ውስጡንም ውጪውንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገለት፤
3
ለመሸከሚያ የሚያገለግሉ አራት የወርቅ ቀለበቶችም አደረገለት፤ እነርሱንም በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች በሌላውም ወገን ሁለት ቀለበቶች በማድረግ በአራቱ እግሮች ላይ አኖራቸው፤
4
መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
5
በታቦቱ ጐንና ጐን ላይ በተሠሩትም ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው።
6
ርዝመቱ መቶ ዐሥር ሳንቲ ሜትር ስፋቱም ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤
7
ክንፍ ያላቸውንም ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሠርቶ፥
8
በመክደኛው ላይ አንዱን በአንድ በኩል፥ ሁለተኛውንም በሌላ በኩል አደረገው፤ ከመክደኛውም ጋር አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው።
9
ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘርግተው መክደኛውን በመሸፈን እርስ በርስ እንዲተያዩ አደረገ።
10
ርዝመቱ ሰማኒያ ስምንት ሳንቲ ሜትር የጐኑ ስፋት አርባ አራት ሳንቲ ሜትር፥ ቁመቱም ስድሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር የሚሆን ጠረጴዛ ከግራር እንጨት ሠራ።
11
በንጹሕም ወርቅ ለብጦ፥ በዙሪያው የወርቅ ክፈፍ አደረገለት።
12
ደግሞም በዙሪያው ሰባ አምስት ሚሊ ሜትር ስፋት ያለው ጠርዝና በጠርዙም ዙሪያ የወርቅ ክፈፍ አደረገለት።
13
አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠርቶ አራቱ እግሮቹ በተተከሉበት አራት ማእዘኖች ላይ አደረገ።
14
ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉ የመሎጊያ ማስገቢያዎቹ ቀለበቶችም በክፈፉ አጠገብ ነበሩ።
15
መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
16
በጠረጴዛው ላይ የሚቀመጡ ልዩ ልዩ የመገልገያ ዕቃዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ ይኸውም፦ የዕጣን ማስቀመጫ ዝርግ ሳሕኖችንና ወጭቶችን፥ ጭልፋዎችን ለወይን ጠጅ መቅጃ የሚሆኑ ማንቈርቈሪያዎችንና ጐድጓዳ ሣሕኖችን ሠራ።
17
መቅረዙንም ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ ማቆሚያውንና ዘንጉንም ከተቀጠቀጠ ወርቅ አበጀ፤ ለጌጥ የሚሆኑትንም የአበባዎች ቅርጽ ከነእንቡጣቸውና ከነቀንበጣቸው አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው።
18
በአንድ በኩል ሦስት፥ በሌላ በኩል ሦስት በመሆን ከጐኖቹ ስድስት ቅርንጫፎች እንዲወጡ አደረገ።
19
ስድስቱም ቅርንጫፎች እያንዳንዱ እንቡጥና ቀንበጥ ያላቸውን የለውዝ አበባዎችን የሚመስሉ ሦስት ሦስት ጌጠኛ የአበባ ወርድ ተስለውበት ነበር።
20
የመቅረዙም ዘንግ እንቡጥና ቀንበጥ ያላቸውን የለውዝ አበባዎችን የሚመስሉ አራት የጌጠኛ አበባ ወርዶች ተስለውበት ነበር።
21
ከሦስቱም ጥንድ ቅርንጫፎች በእያንዳንዱ ጥንድ ሥር አንድ እንቡጥ ተስሎ ነበር፤
22
እንቡጦቹ ቅርንጫፎቹና መቅረዙ ከተቀጠቀጠ ወርቅ አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ።
23
ለመቅረዙም ሰባት መብራቶችን፥ መኰስተሪያዎችንና የኲስታሪ ማኖሪያዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
24
መቅረዙንና የእርሱን መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ለመሥራት የፈጀበት የወርቅ መጠን ሠላሳ አምስት ኪሎ ግራም ነበር።
25
ርዝመቱ አርባ አምስት ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑ ስፋት አርባ አምስት ሳንቲ ሜትር ቁመቱም ዘጠና ሳንቲ ሜትር የሆነ አራት ማእዘን የዕጣን መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ፤ በአራቱም ማእዘን ያሉት ጒጦቹ ከእርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ።
26
ጫፉን፥ አራት ጐኖቹንና ጒጦቹን ሁሉ በንጹሕ ወርቅ ለበጠ፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት።
27
ከክፈፉም ሥር ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አደረገ፤ በሁለቱም ጐን ግራና ቀኝ አኖራቸው፤ እነርሱም የዕጣን መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉ መሎጊያዎች የሚሾልኩባቸው ነበሩ።
28
መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
29
የተቀደሰውን የቅባት ዘይትና መልካም መዓዛ ያለውንም ጥሩ ዕጣን እንደ ሽቶ ቀላቅሎ ሠራ።
← Chapter 36
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 38 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40