bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Bible (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
/
Job 21
Job 21
Amharic Bible (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
← Chapter 20
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 22 →
1
ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ።
2
ስሙ፥ ቃሌን ስሙ፤ ይህም መጽናናታችሁ ይሁን።
3
እናገር ዘንድ ተዉኝ፤ ከተናገርሁም በኋላ ተሳለቁ።
4
በውኑ የኀዘን እንጉርጕሮዬ ለሰው እናገራለሁን? አለመታገሥ ስለ ምን አይገባኝም?
5
ወደ እኔ ተመልከቱ፥ ተደነቁም፤ እጃችሁንም በአፋችሁ ላይ አኑሩ።
6
እኔ ባሰብሁ ቍጥር እጨነቃለሁ፥ ፃዕርም ሥጋዬን ይይዛል።
7
ስለ ምን ኃጢአተኞች በሕይወት ይኖራሉ? ስለ ምንስ ያረጃሉ? በባለጠግነትስ ስለ ምን ይበረታሉ?
8
ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ጸንቶ ይኖራል፥ ልጆቻቸውም በዓይናቸው ፊት ናቸው።
9
ቤታቸው ከፍርሃት ወጥቶ የታመነ ነው፥ የእግዚአብሔርም በትር የለባቸውም።
10
ኮርማቸው ይወልዳል፥ ዘሩንም አይጥለውም፤ ላማቸውም ትወልዳለች፥ አትጨነግፍም።
11
ሕፃናቶቻቸውን እንደ መንጋ ያወጣሉ፥ ልጆቻቸውም ይዘፍናሉ።
12
ከበሮና መሰንቆ ወስደው ይዘምራሉ፥ በእምቢልታ ድምፅ ደስ ይላቸዋል።
13
ዕድሜያቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ፤ ድንገትም ወደ ሲኦል ይወርዳሉ።
14
እግዚአብሔርንም። ከእኛ ዘንድ ራቅ፤ መንገድህን እናውቅ ዘንድ አንወድድም።
15
እናመልከውስ ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወይስ ወደ እርሱ ብንጸልይ ምን ይጠቅመናል? ይላሉ።
16
እነሆ፥ ሀብታቸው በእጃቸው ውስጥ አይደለምን? የኃጥአን ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት።
17
የኃጥአን መብራት የጠፋው፥ መቅሠፍትም የመጣባቸው፥ እግዚአብሔርም በቍጣው መከራ የከፈላቸው፥
18
በነፋስ ፊት እንደ ገለባ፥ ዐውሎ ነፋስም እንደሚወስደው ትቢያ የሆኑ ስንት ጊዜ ነው?
19
እናንተ። እግዚአብሔር በደላቸውን ለልጆቻቸው ይጠብቃል ብላችኋል። እነርሱ ያውቁ ዘንድ ፍዳን ለራሳቸው ይክፈል።
20
ዓይኖቻቸው ጥፋታቸውን ይዩ፥ ሁሉን ከሚችል አምላክ ቍጣ ይጠጡ።
21
የወራታቸውስ ቍጥር ቢቈረጥ፥ ከእነርሱ በኋላ የቤታቸው ደስታ ምን ይሆናቸዋል?
22
ከፍ ከፍ ባሉትስ ላይ ለሚፈርድ ለእግዚአብሔር በውኑ ሰው እውቀትን ያስተምራልን?
23
አንድ ሰው በሰላም ተዘልሎ ሲቀመጥ በሙሉ ኃይሉ ሳለ ይሞታል።
24
በአንጀቱ ውስጥ ስብ ሞልቶአል፥ የአጥንቶቹም ቅልጥም ረጥቦአል።
25
ሌላውም ሰው መልካምን ነገር ከቶ ሳይቀምስ በተመረረች ነፍስ ይሞታል።
26
በአፈር ውስጥ በአንድ ላይ ይተኛሉ፥ ትልም ይከድናቸዋል።
27
እነሆ፥ አሳባችሁን፥ የመከራችሁብኝንም ክፉ ምክር አውቄዋለሁ።
28
እናንተ። የከበርቴው ቤት የት ነው? ኃጢአተኛውም ያደረበት ድንኳን የት ነው? ብላችኋል።
29
መንገድ አላፊዎችን አልጠየቃችሁምን? ምልክታቸውን አታውቁምን?
30
ኃጢአተኛው በመቅሠፍት ቀን እንደ ተጠበቀ፥ በቍጣው ቀን እንደሚድን።
31
መንገዱን በፊቱ የሚናገር ማን ነው? የሠራውንስ የሚመልስበት ማን ነው?
32
እርሱን ግን ወደ መቃብር ይሸከሙታል፥ ሰዎቹም በመቃብሩ ላይ ይጠብቃሉ።
33
የሸለቆው ጓል ይጣፍጥለታል፤ በኋላውም ሰው ሁሉ ይሳባል፥ በፊቱም ቍጥር የሌለው ጉባኤ አለ።
34
የምትመልሱልኝ ውስልትና ነውና በከንቱ እንዴት ታጽናኑኛላችሁ?
← Chapter 20
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 22 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42