bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Bible (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
/
Job 3
Job 3
Amharic Bible (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 4 →
1
ከዚያም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ።
2
ኢዮብም መለሰ እንዲህ አለ።
3
ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ ያም። ወንድ ልጅ ተፀነሰ የተባለበት ሌሊት።
4
ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፥ ብርሃንም አይብራበት።
5
ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፤ ዳመናም ይረፍበት፤ የቀን ጨለማ ሁሉ ያስፈራው።
6
ያን ሌሊት ጨለማ ይያዘው፤ በዓመቱ ቀኖች መካከል ደስ አይበለው፤ በወሮች ውስጥ ገብቶ አይቈጠር።
7
እነሆ፥ ያ ሌሊት መካን ይሁን፤ እልልታ አይግባበት።
8
ሌዋታንን ለማንቀሳቀስ የተዘጋጁ ቀኑን የሚረግሙ ይርገሙት።
9
አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፤ ብርሃንን ቢጠባበቅ አያግኘው፥ የንጋትንም ቅንድብ አይይ፤
10
የእናቴን ማኅፀን ደጅ አልዘጋምና፥ መከራንም ከዓይኔ አልሰወረምና።
11
በማኅፀን ሳለሁ ስለ ምን አልሞትሁም? ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ፈጥኜ ስለ ምን አልጠፋሁም?
12
ጕልበቶች ስለ ምን ተቀበሉኝ? ጡትስ ስለ ምን ጠባሁ?
13
አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፤ አንቀላፍቼ ባረፍሁ ነበር፤
14
የፈረሰውን ለራሳቸው ከሚሠሩት ከምድር ነገሥታትና መካሮች ጋር፥
15
ወይም ቤታቸውን ብር ከሞሉ ወርቅም ካላቸው መኳንንት ጋር፥
16
ወይም እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ፥ ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።
17
ክፉዎች በዚያ መናደዳቸውን ይተዋሉ፤ በዚያም ደካሞች ያርፋሉ።
18
በዚያ ግዞተኞች በአንድነት ተዘልለው ተቀምጠዋል፤ የአስጨናቂውን ድምፅ አይሰሙም።
19
ታናሽና ታላቅ በዚያ አሉ፤ ባሪያም ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።
20
በመከራ ላሉት ብርሃን፥ ነፍሳቸው መራራ ለሆነችባቸው፥
21
የተሰወረ ሀብትን ከሚቈፍሩ ይልቅ ሞትን ለሚጠብቁ ለማያገኙትም፥
22
መቃብርን ባገኙ ጊዜ በእልልታ ደስ ለሚላቸው፥ ሐሤትንም ለሚያደርጉ ሕይወት ስለ ምን ተሰጠ?
23
መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፥ እግዚአብሔርም በአጥር ላጠረው ብርሃን ስለ ምን ተሰጠ?
24
ከእንጀራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ጩኸቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል።
25
የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።
26
ተዘልዬ አልተቀመጥሁም፥ አልተማመንሁም፥ አላረፍሁም፤ ነገር ግን መከራ መጣብኝ።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42