bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
2 Chronicles 11
2 Chronicles 11
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 10
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 12 →
1
ሮብዓምም ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ እስራኤልን ወግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም ይመልሱ ዘንድ ከይሁዳና ከብንያም ቤት የተመረጡትን አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰልፈኞች ጐልማሶችን ሰበሰበ።
2
የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሰማያ እንዲህ ሲል መጣ፦
3
“ለይሁዳ ንጉሥ ለሰሎሞን ልጅ ለሮብዓም፥ በይሁዳና በብንያምም ላሉት ለእስራኤል ሁሉ፦
4
‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አትውጡ፤ ወንድሞቻችሁንም አትውጉ፤ እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ይመለስ’ ብለህ ንገራቸው።” የእግዚአብሔርንም ቃል ሰሙ፤ በኢዮርብዓምም ላይ ከመሄድ ተመለሱ።
5
ሮብዓምም በኢየሩሳሌም ተቀመጠ፤ በይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች ሠራ።
6
በይሁዳና በብንያም ያሉትንም የተመሸጉትን ከተሞች፥ ቤተ ልሔምን፥ ኤጣምን፥ ቴቁሔን፤
7
ቤተሱራን፥ ሱላኮን፥ ዓዶላምን፥
8
ጌትን፥ መሪሳን፥ ዚፍን፥
9
አዶራይምን፥ ለኪስን፥ ዓዚቃን፤
10
ሶርዓን፥ ኤሎንን፥ ኬብሮንን ሠራ።
11
ምሽጎቹንም አጠነከረ፤ አለቆችንም አኖረባቸው፤ ምግቡንም፥ ዘይቱንም፥ የወይን ጠጁንም አከማቸባቸው።
12
በከተሞቹ ሁሉ አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦርን አኖረ፤ ከተሞቹንም እጅግ አጠነከራቸው፤ ይሁዳና ብንያምም የእርሱ ወገን ነበሩ።
13
በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ የነበሩ ካህናትና ሌዋውያን ከየሀገራቸው ሁሉ ወደ እርሱ መጡ።
14
የእግዚአብሔርም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰምሪያቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
15
እርሱ ግን ለኮረብታው መስገጃዎች፥ ከንቱ ለሆኑ ጣዖታቱም፥ ኢዮርብዓም ለሠራቸው እንቦሶችም ካህናትን አቆመ።
16
ደግሞም ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልባቸውን የሰጡ ሁሉ እነርሱን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
17
ሦስት ዓመትም በዳዊትና በሰሎሞን መንገድ ይሄድ ነበርና ሦስት ዓመት የይሁዳን መንግሥት አበረቱ፤ የሰሎሞንንም ልጅ ሮብዓምን አጸኑ።
18
ሮብዓምም የዳዊትን ልጅ የኢያሪሙትን ሴት ልጅ ሞላትን አገባ፤ እናቷም የእሴይ ልጅ የኤልያብ ልጅ አቢካኤል ነበረች።
19
እርስዋም የዑስን፥ ሰማርያንና፥ ዘሃምን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።
20
ከእርስዋም በኋላ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ፤ እርስዋም አብያን፥ ኢያቲን፥ ዚዛን፥ ሰሎሚትን ወለደችለት።
21
ሮብዓምም ከሚስቶቹና ከቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን ወደደ፤ ዐሥራ ስምንትም ሚስቶችና ስድሳ ቁባቶች ነበሩት፤ ሃያ ስምንት ወንዶችና ስድሳ ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
22
ሮብዓምም ያነግሠው ዘንድ አስቦአልና የመዓካን ልጅ አብያን በወንድሞቹ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው።
23
ብልሃተኛም ሆነ፤ ልጆቹንም ሁሉ በይሁዳና በብንያም ሀገር ሁሉ በምሽጉ ከተሞች ሁሉ ከፋፈላቸው፤ ብዙም ምግብ ሰጣቸው፤ ብዙም ሚስቶች ፈለገላቸው።
← Chapter 10
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 12 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36