bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
2 Chronicles 8
2 Chronicles 8
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 7
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 9 →
1
እንዲህም ሆነ፤ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት የሠራበት ሃያ ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፥
2
ኪራም ለሰሎሞን የሰጠውን ከተሞች ሰሎሞን ሠራቸው፤ የእስራኤልንም ልጆች አኖረባቸው።
3
ሰሎሞንም ወደ ኤማትሱባ ሄደ፤ በረታባትም።
4
በምድረ በዳም ያለውን ተድሞርን፥ በኤማትም የጸኑ ከተሞችን ሁሉ ሠራ።
5
ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ፥ መወርወሪያም የነበራቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ላይኛውን ቤትሖርን፥ ታችኛውንም ቤትሖርን ሠራ።
6
ባዕላትንም፥ ለሰሎሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፥ የሰረገላውንም ከተሞች ሁሉ፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም፥ በሊባኖስም፥ በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ይሠራ ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠራ።
7
ከኬጤዎናውያን፥ ከአሞሬዎናውያን፥ ከፌርዜዎናውያንም፥ ከኤዎናውያንም፥ ከኢያቡሴዎናውያንም የቀሩትን፥ ከእስራኤል ወገን ያልሆኑትን ሕዝብ ሁሉ፥
8
የእስራኤልም ልጆች ያላጠፉአቸውን፥ በኋላቸውም በምድር ላይ የቀሩትን ልጆቻቸውን ሰሎሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አደረጋቸው።
9
ሰሎሞንም በመንግሥቱ ከእስራኤል ልጆች ማንንም አገልጋይ አላደረገም፤ እነርሱ ሰልፈኞች፥ የሹሞችም አለቆች፥ የሰረገሎችና የፈረሰኞች ባልደራሶች ነበሩና።
10
እነዚህም በሕዝቡ ላይ ያለውን ሥራ የሚቈጣጠሩ የንጉሡ የሰሎሞን ዓይነተኞች አለቆች ሁለት መቶ አምሳ ነበሩ።
11
ሰሎሞንም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት የገባችበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም” ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ወደ ሠራላት ቤት አወጣት።
12
በዚያ ጊዜም ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት ፊት በሠራው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።
13
ሙሴም እንዳዘዘ እንደ ሥርዐታቸው በየቀኑ ሁሉ፥ በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየበዓላቱም፥ በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓልና በየሰባቱ ሱባዔ በዓል፥ በየዳሱም በዓል ቍርባን ያቀርቡ ነበር።
14
የእግዚአብሔርም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዐት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዐታቸው ያመሰግኑ ዘንድ፥ በካህናቱም ፊት ያገለግሉ ዘንድ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ በረኞቹንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።
15
እነርሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝገቡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አልተላለፉም።
16
እነሆ፥ መሠረቱ ከተጣለ ጀምሮ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት እስከ ፈጸመ ድረስ ሥራው ሁሉ የተዘጋጀ ነበረ። የእግዚአብሔርም ቤት ተፈጸመ።
17
ሰሎሞንም የዚያን ጊዜ በኤዶምያስ ምድር በባሕር ዳር ወዳሉ ወደ ጋሴዎንጋብርና ወደ ኤላት ሄደ።
18
ኪራምም መርከቦችንና የባሕርን ነገር የሚያውቁትን መርከበኞች በአገልጋዮቹ እጅ ላከለት፤ እነርሱም ከሰሎሞን አገልጋዮች ጋር ወደ ሴፌር መጡ፤ ከዚያም አራት መቶ አምሳ መክሊት ወርቅ ወስደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን አመጡ።
← Chapter 7
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 9 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36