bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
2 Chronicles 4
2 Chronicles 4
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 5 →
1
ርዝመቱም ሃያ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመቱም ዐሥር ክንድ የነበረውን የናሱን መሠዊያ ሠራ።
2
ዳግመኛም ከቀለጠ ናስ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፥ ቁመትዋም አምስት ክንድ፥ ዙሪያዋም ሠላሳ ክንድ የሆነ ኵሬ ሠራ።
3
በበታችዋም፥ በዙሪያዋ በዐሥሩ ክንድ የበሬዎች ምስሎች ነበሩ። ኵሬዋንም ይከብቡአት ነበር። በሬዎቹም በሁለት ተራ ሁነው ከኵሬው ጋር በአንድነት ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ።
4
ዐሥራ ሁለት በሬዎችን ሠሩላቸው። ከእነርሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፥ ሦስቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስቱም ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር፤ ቀልጣ የተሠራች ኵሬም በላያቸው ነበረች፤ የሁሉም ጀርባቸው በስተውስጥ ነበረ።
5
ውፍረትዋም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከንፈሯም እንደ ጽዋ ከንፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም ማድጋ ትይዝ ነበር ሠርቶም ፈጸማት፤
6
ደግሞም ዐሥር የመታጠቢያ ሰኖችን ሠራ፤ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው ነገር ሁሉ ይታጠብባቸው ዘንድ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ባሕሩ ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር።
7
ዐሥሩንም የወርቅ መቅረዞች እንደ ሥርዐታቸው ሠራ፤ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ በመቅደሱ ውስጥ አኖራቸው።
8
ዐሥሩንም የወርቅ ገበታዎች ሠርቶ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ በመቅደሱ ውስጥ አኖራቸው። አንድ መቶም የወርቅ ጽዋዎችን ሠራ።
9
ደግሞም የካህናቱን አደባባይ ፥ ታላቁንም አደባባይ፥ የአደባባዩንም ደጆች ሠራ፤ ደጆቻቸውንም በናስ ለበጠ።
10
ኵሬውንም በቤተ መቅደሱ መዓዝን በስተቀኝ በኩል በምሥራቅ አቅጣጫ አኖረው።
11
ኪራምም ምንቸቶቹንና መጫሪያዎቹን፥ በመሠዊያው ቤት ያሉ ማንኪያዎችንና የመገልገያውን ዕቃ ሁሉ ሠራ። ኪራምም ለንጉሡ ለሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።
12
ሁለት ዐምዶችንና በሁለቱ ዐምዶች ላይ ጕልላቶችን፥ በዐምዶቹም ራሶች ላይ ያሉትን ጕልላቶች የሚሸፍኑ ሁለት መርበቦችን ሠራ።
13
በሁለቱም መርበቦች አራት መቶ የወርቅ ሻኵራዎችንና በዐምዶቹ ላይ ያሉትን ሁለት ጕልላቶች በሁለት ጎኖች የሚሸፍኑትን ሮማኖች ሠራ።
14
ዐሥር መቀመጫዎችንና በመቀመጫዎቹም ላይ መታጠቢያዎችን ሠራ፤
15
አንድዋንም ኵሬ፥ በበታችዋም ያሉትን ዐሥራ ሁለት በሬዎች ሠራ።
16
የእግር መታጠቢያዎችን፥ የእጅ መታጠቢያዎችን፥ ጋኖችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜንጦዎችንና ኪራም የሠራውን ሥራ ሁሉ ከንጹሕ ናስ ሠርቶ ለንጉሡ ለሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት አቀረበለት።
17
ንጉሡም በዮርዳኖስ ሜዳ በሱኮትና በሴድራ መካከል ባለው በወፍራሙ መሬት ውስጥ አቀለጣቸው።
18
ሰሎሞንም እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ እጅግ አብዝቶ ሠራ፤ የናሱም ብዛት አይቈጠርም ነበር።
19
ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን ዕቃ ሁሉ፥ የወርቁንም መሠዊያ፥ ኅብስተ ገጽ የነበረባቸውን ገበታዎች ሠራ።
20
በመቅደሱ ፊት እንደ ሥርዐታቸው የሚያበሩ መቅረዞችንና ቀንዲሎችንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።
21
የመብራቶች መቅረዞችንና በላያቸው ያሉ መብራቶችን፥ ጽዋዎቹን፥ ማንኪያዎቹን፥ ሥራ የሚሠሩባቸው ጻሕሎችንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።
22
ውስጠኛው የእግዚአብሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ የሚወስደው የውስጠኛውም የቤተ መቅደሱ ደጆች የወርቅ ነበሩ። እንዲሁም ሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ።
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 5 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36