bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Exodus 18
Exodus 18
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 17
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 19 →
1
የምድያም ካህን የሙሴ አማት ዮቶር እግዚአብሔር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እስራኤልን ከግብፅ እንደ አወጣ ሰማ።
2
በዚያ ጊዜ የሙሴ አማት ዮቶር ትቶአት የነበረውን የሙሴን ሚስት ሲፓራን፥ ሁለቱንም ልጆችዋን ወሰደ።
3
የአንደኛው ስም ጌርሳም ነበረ፤ አባቱ “በሌላ ሀገር ስደተኛ ነበርሁ” ብሎአልና፤
4
የሁለተኛውም ስም አልዓዛር ነበረ፤ “የአባቴ አምላክ ረዳኝ፤ ከፈርዖንም እጅ አዳነኝ” ብሎአልና።
5
የሙሴ አማት ዮቶርም ከልጆቹና ከሚስቱ ጋር በእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ በምድረ በዳ ወደ ሰፈረ ወደ ሙሴ መጣ።
6
ሙሴንም፥ “እነሆ፥ አማትህ ዮቶር፥ ሚስትህም ከእርስዋም ጋር ሁለቱ ልጆችህ መጥተውልሃል” አሉት።
7
ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ፤ እጅ ነሣው፤ ሳመውም፤ እርስ በርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጡ፤ ወደ ድንኳኑም ገቡ።
8
ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እንደ አዳናቸው ለአማቱ ነገረው።
9
ዮቶርም እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ እንደ አዳናቸው ሰምቶ በሁሉ አደነቀ።
10
ዮቶርም፥ “ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ ሕዝቡን የአዳነ እግዚአብሔር ቡሩክ ነው።
11
እግዚአብሔርም ግብፃውያን ከሚመኩባቸውና ከሚገዙላቸው አማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አሁን ዐወቅሁ” አለ።
12
የሙሴ አማት ዮቶርም የሚቃጠል መሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እንጀራ ሊበሉ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ።
13
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ በሕዝቡ ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር።
14
ዮቶርም ሙሴ በሕዝቡ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቶ እንዲህ አለው፥ “ብቻህን ተቀምጠህ በሕዝቡ የምታደርገው ይህ ምንድን ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙሪያህ ቆመዋል።”
15
ሙሴም አማቱን፥ “ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ፍርድ ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ፤
16
ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፤ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ሥርዐትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ” አለው።
17
የሙሴም አማት አለው፥ “አንተ የምታደርገው ይህ ነገር ትክክል አይደለም።
18
አንተ፥ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ ይህ ነገር ይከብድብሃል፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም።
19
አሁንም እመክርሃለሁና ስማኝ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝቡ ሁን፤ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አድርስ፤
20
የእግዚአብሔርንም ሥርዐቱንና ሕጉን መስክርላቸው፤ የሚሄዱበትንም መንገድ፥ የሚያደርጉትንም ሥራ ሁሉ አሳያቸው።
21
አንተም ከሕዝቡ ሁሉ ኀያላን ሰዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን እውነተኞች ሰዎችን፥ ትዕቢትንም የሚጠሉ ሰዎችን ፈልግ። ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የዐሥርም አለቆችን ሹምላቸው።
22
በሕዝቡ ላይ ሁል ጊዜ ይፍረዱ፤ የከበዳቸውን ነገር ወደ አንተ ያምጡት፤ ቀላሉን ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ ያቃልሉልሃል፤ ይረዱሃልም።
23
ይህንም ቃሌን ብታደርግ፥ እግዚአብሔር ያበረታሃል፤ መፍረድም ትችላለህ፤ ሕዝቡም ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው ይመለሳል።”
24
ሙሴም የአማቱን ቃል ሰማ፤ እንደ አለውም አደረገ።
25
ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳም አለቆች፥ የዐሥርም አለቆች አድርጎ ሾማቸው።
26
በሕዝቡም ላይ ሁልጊዜ ፈረዱ፤ የከበዳቸውንም ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፤ ቀላሉን ነገር ሁሉ ግን እነርሱ ፈረዱ።
27
ሙሴም አማቱን አሰናበተው፤ እርሱም ወደ ሀገሩ ተመለሰ።
← Chapter 17
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 19 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40