bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Exodus 2
Exodus 2
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 3 →
1
ከሌዊ ወገን እንበረም የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከሌዊ ሴቶች ልጆች ሚስትን አገባ።
2
ሴቲቱም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ መልካምም እንደሆነ በአዩ ጊዜ ሦስት ወር ሸሸጉት።
3
ደግሞም ሊሸሽጉት በአልቻሉ ጊዜ እናቱ የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም አኖረችበት፤ በወንዝም ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው።
4
እኅቱም ምን እንደሚደርስበት ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትጐበኘው ነበር።
5
የፈርዖንም ሴት ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ደንገጥሮችዋም በወንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥኑንም በቄጠማ ውስጥ አየች፤ ደንገጥርዋንም ልካ አስመጣችው።
6
ሣጥኑን በከፈተችም ጊዜ ሕፃኑን አየች፤ እነሆም፥ ሕፃኑ በሣጥኑ ውስጥ ያለቅስ ነበር፤ የፈርዖንም ልጅ አዘነችለት፥ “ይህ ሕፃን ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች።
7
የዚያም ሕፃን እኅት ለፈርዖን ልጅ፥ “ሕፃኑን ታጠባልሽ ዘንድ ሄጄ የምታጠባ ሴት ከዕብራውያን ሴቶች ልጥራልሽን?” አለቻት።
8
የፈርዖንም ልጅ፥ “ሂጂና ጥሪልኝ” አለቻት፤ ብላቴናዪቱም ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራች።
9
የፈርዖንም ልጅ፥ “ይህን ሕፃን ተንከባክበሽ አጥቢልኝ፤ ዋጋሽንም እሰጥሻለሁ” አለቻት። ሴቲቱም ሕፃኑን ወስዳ አጠባችው።
10
ሕፃኑም በአደገ ጊዜ ወደ ፈርዖን ልጅ ወሰደችው፤ ለእርስዋም ልጅ ሆነላት። እኔ ከውኃ አውጥቼዋለሁና ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው ።
11
ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አደገ፤ ወደ ወንድሞቹም ወጣ፤ መከራቸውንም ተመለከተ፤ የግብፅም ሰው ከወንድሞቹ ከእስራኤል ልጆች አንዱን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ።
12
ወዲህና ወዲያ ተመለከተ፤ ማንንም አላየም፤ ግብፃዊውንም ገደለው፤ በአሸዋ ውስጥም ቀበረው።
13
በሁለተኛውም ቀን ወጣ፤ ሁለቱም የዕብራውያን ሰዎች ሲጣሉ አየ፤ ሙሴም በዳዩን፥ “ለምን ባልንጀራህን ትመታዋለህ?” አለው።
14
ወንድሙን የሚበድለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ? ወይስ ግብፃዊውን ትናንት እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአልን?” ብሎ ፈራ።
15
ፈርዖንም ይህን ነገር ሰማ፤ ሙሴንም ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፤ በምድያምም ምድር ተቀመጠ፤ ወደ ምድያም ምድር በደረሰ ጊዜም በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ዐረፈ።
16
ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ይጠብቁ ነበር፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ሊያጠጡ የውኃዉን ገንዳ ሞሉ።
17
እረኞችም መጥተው ገፉአቸው፤ ሙሴ ግን ተነሥቶ አዳናቸው፤ እየቀዳም በጎቻቸዉን አጠጣላቸው።
18
ወደ አባታቸውም ወደ ራጉኤል መጡ እርሱም፥ “ዛሬስ እንዴት ፈጥናችሁ መጣችሁ?” አላቸው።
19
እነርሱም፥ “አንድ የግብፅ ሰው ከእረኞች እጅ አዳነን፤ ደግሞም ቀዳልን፤ በጎቻችንንም አጠጣልን” አሉት።
20
ልጆቹንም፥ “ሰውዬው ወዴት ነው? ለምንስ ያን ሰው ተዋችሁት? ጥሩት፤ እንጀራም ይብላ” አላቸው።
21
ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ሊቀመጥ ወደደ፤ ልጁንም ሲፓራን ለሙሴ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው።
22
ያችም ሴት ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ ሙሴም፥ “በሌላ ምድር መጻተኛ ነኝ” ሲል ስሙን ጌርሳም ብሎ ጠራው። ዳግመኛም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ኤልኤዜር አለው፤ የአባቴ ፈጣሪ ረዳቴ ነው ሲል።
23
ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለ ባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።
24
እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ሰማ፤ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ፥ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ዐሰበ።
25
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች ጐበኛቸው፤ ታወቀላቸውም።
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40