bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Exodus 38
Exodus 38
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 37
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 39 →
1
ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆን መሠዊያን ከማይነቅዝ ዕንጨት አደረገ፤ አራት ማዕዘንም ነበረ፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ነበረ።
2
ቀንዶቹንም በአራቱ ማዕዘን አደረገበት፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ በናስም ለበጠው።
3
የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ሜንጦዎቹንም፥ የእሳት ማንደጃዎቹንም አደረገ፤ ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አደረገ።
4
እንደ መረብ ሆኖም የተሠራ የናስ መከታ ለመሠዊያው አደረገ፤ መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ ይደርስ ዘንድ በመሠዊያው በሚዞረው በደረጃው ታች አደረገው።
5
ለናሱም መከታ ለአራቱ ማዕዘን የመሎጊያዎች ስፍራ ይሆኑ ዘንድ አራት ቀለበቶች አደረገ።
6
መሎጊያዎቹንም ከማይነቅዝ ዕንጨት ሠራ፤ በናስም ለበጣቸው።
7
ይሸከሙባቸውም ዘንድ በመሠዊያው ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ መሎጊያዎቹን አገባ፤ ከሳንቃዎቹም ሠርቶ ክፍት አደረገው።
8
የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውንም በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ከሴቶች መስተዋት ከናስ አደረገ።
9
ለድንኳኑም በደቡብ በኩል በስተቀኝ አደባባይ አደረገ፤ የአደባባዩ መጋረጃም ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ ርዝመቱ መቶ ክንድ ነበረ።
10
ሃያውንም ምሰሶዎቻቸውንና ሃያውን እግሮቻቸውን ከናስ አደረገ፤ የምሰሶዎቹንም ኵላቦችና ዘንጎች ከብር አደረገ።
11
በሰሜኑም ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎች፥ ከናስም የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎችንና ሃያ እግሮችን፥ ለምሰሶዎችም የብር ኵላቦችንና ዘንጎችን አደረገ።
12
በምዕራብም ወገን አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎች፥ ዐሥሩንም ምሰሶዎች፥ ዐሥሩንም የናስ እግሮች፥ ለምሰሶዎቹም የብር ኵላቦችንና ዘንጎችን አደረገ።
13
በምሥራቅም ወገን አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎችን አደረገ።
14
በአዜብ በኩል የመጋረጃዎች ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ፥ ምሰሶዎቹም ሦስት፥ እግሮቹም ሦስት ነበሩ።
15
እንዲሁም በሁለተኛው ወገን በአደባባዩ ደጅ በዚህና በዚያ ዐሥራ አምስት ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ሦስትም ምሰሶዎች፥ ሦስትም እግሮች ነበሩ።
16
በአደባባዩ ዙሪያ ያሉ መጋረጃዎች ሁሉ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ ተሠርተው ነበር።
17
የምሰሶዎቹም እግሮች የናስ፥ የምሰሶዎቹም ኵላቦችና ዘንጎች የብር ነበሩ፤ የምሰሶዎቹም ጕልላቶች በብር ተለብጠው ነበር፤ በአደባባዩ ላሉ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሩአቸው።
18
የአደባባዩም ደጅ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ፥ ከጥሩም በፍታ በጥልፍ አሠራር የተሠራ ነበረ፤ ርዝመቱ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ቁመቱም እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች አምስት ክንድ ነበረ፤
19
ከናስ የተሠሩ ምሰሶዎቹም አራት፥ እግሮቹም አራት ነበሩ፤ ኵላቦቹም የብር ነበሩ፤ ጕልላቶቹና ዘንጎቹም በብር ተለብጠው ነበር።
20
የድንኳኑም ካስማዎች፥ በዙሪያውም ያሉ የአደባባዩ ካስማዎች የናስ ነበሩ።
21
በካህኑ በአሮን ልጅ በይታምር እጅ የሌዋውያን ተልእኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእግዚአብሔር እንደታዘዘ የምስክሩ ድንኳን ሥርዐት ይህ ነው።
22
ከይሁዳ ነገድም የሆነ የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤል እግዚአብሔር ለሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ።
23
ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነ የአሒሳሚክ ልጅ ኤልያብ ነበረ፤ እርሱም በሰማያዊ፥ በሐምራዊ፥ በቀይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍታ የሽመና ሥራ ይሠራ ዘንድ የቅርጽ፥ የሽመናና የጥልፍ ሥራ አለቃ ነበረ።
24
የተሰጠው ወርቅ ሁሉ፥ ለድንኳኑ ሥራ ሁሉ የተደረገው ወርቅ፥ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ሃያ ዘጠኝ መክሊት ሰባት መቶ ሠሳሳ ሰቅል ነበረ።
25
በማኅበሩም ከሚቈጠሩት የተገኘ ብር፥ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን፥ መቶ መክሊትና አንድ ሺህ ሰባት መቶ ከሰባ አምስት ሰቅል ነበረ።
26
እያንዳንዱም ሰው አንድ አንድ ዲድርክም አዋጣ፤ አንድ ዲድርክም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ነው፤ ይህም የተዋጣው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ከተቈጠሩ ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበረ።
27
መቶውም የብር መክሊት ለድንኳኑ ምሰሶዎች እግሮችና ለመጋረጃው ምሰሶዎች እግሮች ተደረገ፤ መቶውም መክሊት ለመቶ እግሮች፤ ለአንድ እግርም አንድ መክሊት ሆነ።
28
ከሺህ ሰባት መቶ ሰባ አምስት ሰቅል የምሰሶዎቹን ኵላቦችና ዘንጎች አደረገ፤ የምሰሶዎቹንም ጕልላቶች ለበጠ።
29
የተሰጠውም ናስ አራት መቶ ሰባ መክሊትና ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።
30
ከእርሱም የምስክሩን ድንኳን ደጃፍ እግሮች፥ የናሱንም መሠዊያ፥ ለእርሱም የሆነውን የናሱን መከታ፥ የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥
31
በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩንም ደጃፍ እግሮች፥ የድንኳኑንም ካስማዎች ሁሉ፥ በአደባባዩ ዙሪያም ያሉትን ካስማዎች ሁሉ አደረገ።
← Chapter 37
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 39 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40