bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Numbers 30
Numbers 30
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 29
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 31 →
1
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ነገዶች አለቆች እንዲህ ብሎ ነገራቸው፥ “እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው።
2
ሰው ሁሉ ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም መሐላን ቢምል፤ ራሱንም ቢለይ፥ ቃሉን አያርክስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ።
3
ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባቷ ቤት ሳለች በብላቴንነቷ ጊዜ ራስዋን ብትለይ፥
4
አባቷም ስእለቷንና ራስዋን የለየችበትን ቢሰማ፥ አባቷም ዝም ቢላት፥ ስእለቷ ሁሉ ይጸናል፤ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል።
5
አባቷ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለቷ፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባቷ ከልክሎአታልና እግዚአብሔር ይቅር ይላታል።
6
“ባል ያገባች ብትሆን፥ በአንደበቷም እንደ ተናገረች ስለ ራስዋ የተሳለችው ስእለት በራስዋ ላይ ቢሆን፥
7
ባልዋም ቢሰማ፥ በሰማበትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእለቷ፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ይጸናሉ።
8
ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለቷና ራስዋን ያሰረችበት መሐላ አይጸኑም፤ ባልዋ ከልክሎአታልና፤ እግዚአብሔርም ይቅር ይላታል።
9
“ባልዋ የሞተባት ወይም የተፋታች ግን ስእለቷና ራስዋን ያሰረችበት መሐላ ይጸኑባታል።
10
ሴትም በባልዋ ቤት ሳለች ብትሳል፥ ወይም ራስዋን በመሐላ ብታስር፥
11
ባልዋም ሰምቶ ዝም ቢላት፥ ባይከለክላትም፥ ስእለቷ ሁሉ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል።
12
ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ስእለቷን ቢከለክላት፥ ስለ ስእለቷ ወይም ራስዋን ስላሰረችበት መሐላ ከአፍዋ የወጣው ነገር አይጸናም፤ ባልዋ ከልክሏታል፤ እግዚአብሔርም ያነጻታል።
13
“ስእለቷን ሁሉ፥ ነፍስዋንም የሚያዋርደውን የመሐላ ማሰሪያ ሁሉ ባልዋ ያጸናዋል፤ ወይም ባልዋ ይከለክለዋል።
14
ነገር ግን በየዕለቱ ዝም ቢላት፥ ስእለቷን ሁሉ፥ በእርስዋም ላይ ያለውን መሐላ ሁሉ ያጸናዋል፤ በሰማበት ቀን ዝም ብሎአታልና አጽንቶታል።
15
ከሰማው በኋላ ግን ቢከለክላት ኀጢአቱን ይሸከማል።”
16
እርስዋ በብላቴንነቷ ጊዜ በአባቷ ቤት ሳለች በአባትና በልጂቱ መካከል፥ ወይም በባልና በሚስት መካከል ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘው ሥርዐት ይህ ነው።
← Chapter 29
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 31 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36