bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Numbers 4
Numbers 4
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 5 →
1
እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦
2
“ከሌዊ ልጆች መካከል በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች የቀዓትን ልጆች ለዩአቸው፤
3
ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በምስክሩ ድንኳን ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡበትን ሁሉ ትለያለህ።
4
በምስክሩ ድንኳን በቅድስተ ቅዱሳኑ ዘንድ የቀዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤
5
ሰፈሩ በተነሣ ጊዜ አሮንና ልጆቹ ገብተው የሚሸፍነውን መጋረጃ ያወርዳሉ፤ የምስክሩንም ታቦት ይጠቀልሉበታል፤
6
በላዩም የአቆስጣውን ቍርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፤ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ያግቡበት፤ መሎጊያዎቹንም ያግቡበት።
7
በኅብስተ ገጹ ገበታ ላይም ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ጭልፋዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለማፍሰስም መቅጃዎቹን ያድርጉበት፤ ሁልጊዜም የሚኖር ኅብስት በእርሱ ላይ ይሁን።
8
በእነርሱም ላይ ቀይ መጐናጸፊያ ይዘርጉ፤ በአቆስጣውም ቍርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት። መሎጊያዎቹንም ያግቡ።
9
ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፤ የሚያበሩባትንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎችዋንም፥ መኰስተሪያዎችዋንም፥ የኵስታሪ ማድረጊያዎችዋንም፥ እርስዋንም ለማገልገል የዘይቱን ማሰሮዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤
10
እርስዋንና ዕቃዎችዋን ሁሉ በአቆስጣ ቍርበት መሸፈኛ ውስጥ ያድርጉ፤ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት።
11
በወርቁም መሠዊያ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በአቆስጣም ቍርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፤ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።
12
በመቅደስም ውስጥ የሚያገለግሉበትን የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ ይውሰዱ፤ በሰማያዊዉም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡት፤ በአቆስጣም ቍርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፤ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት።
13
አመዱንም ያስወግዱ፤ መክደኛውንም በመሠዊያው ላይ ያድርጉ፤ ሐምራዊዉንም መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤
14
የሚያገለግሉበትን ዕቃውን ሁሉ፥ ማንደጃዎቹን፥ ሜንጦዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ መክደኛዎቹንም፥ ያመድ ማፍሰሻዎቹን፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም የአቆስጣን ቍርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፤ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። ሐምራዊዉንም መጐናጸፊያ ወስደው ማስታጠቢያውንና ማስቀመጫውን ይሸፍኑት፤ በአቆስጣው ቍርበት መሸፈኛ ውስጥም አድርገው በመሸከሚያዎቹ ላይ ያኑሩት፤
15
አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይገባሉ። እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በምስክሩ ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።
16
የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት በጣፋጩም ዕጣን ላይ ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቍርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ሹም ነው፤ ድንኳኑን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይጠብቃል።”
17
እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦
18
“የቀዓትን ወገኖች ነገድ ከሌዋውያን መካከል አታጥፉአቸው፤
19
ነገር ግን ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ በቀረቡ ጊዜ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እንዳይሞቱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ አሮንና ልጆቹ ይግቡ፤
20
ከእነርሱ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራውንና ሸክሙን ያዘጋጁ፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋየ ቅዱሳቱን ለድንገት እንኳን ለማየት አይግቡ።”
21
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
22
“የጌድሶንን ልጆች ከመጀመሪያው ጀምረህ በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገኖቻቸውም ቍጠራቸው።
23
የምስክሩን ድንኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠራቸው።
24
የጌድሶን ወገኖች ሥራ በማገልገልና በመሸከም ይህ ነው፤
25
የድንኳኑን መጋረጃዎች፥ የምስክሩንም ድንኳን፥ መደረቢያውን፥ በላዩም ያለውን የአቆስጣውን ቍርበት መደረቢያ፥ የምስክሩንም ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥ የአደባባዩንም መጋረጃ፥
26
በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፥ ለማገልገልም የሚሠሩበትን ዕቃ ሁሉ ይሸከሙ፤ በዚህም ያገልግሉ።
27
የጌድሶን ልጆች አገልግሎት ሁሉ፥ በተራቸውም ሁሉ፥ በሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ በስማቸውና በተራቸውም ትቈጥራቸዋለህ።
28
የጌድሶን ልጆች አገልግሎት በምስክሩ ድንኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች ይሆናሉ።
29
“የሜራሪንም ልጆች በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች ቍጠራቸው።
30
የምስክሩን ድንኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠራቸው።
31
በምስክሩ ድንኳን ዘንድ ባለው አገልግሎታቸው ሁሉ፥ የድንኳኑ ሳንቆች፥ መወርወሪያዎቹም፥ ተራዳዎቹም፥ እግሮቹም፥ መሸፈኛዎቹም፥ መቀመጫዎቹም፥ የምስክሩ ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥
32
በዙሪያውም የሚቆሙት የአደባባዩ ምሰሶዎች፥ እግሮቹም፥ የአደባባዩ ደጃፍ መጋረጃ ምሰሶዎች፥ እግሮቻቸውም፥ ካስማዎቹም፥ አውታሮቹም፥ ዕቃዎቹና ማገልገያዎቹ ሸክማቸው ነው፤ የሚጠብቁትንም የሸክማቸውን ዕቃ ሁሉ በየስማቸው ቍጠሩ።
33
በምስክሩ ድንኳን ዘንድ ባለው ሥራቸው ሁሉ የሜራሪ ልጆች ወገኖች አገልግሎት ይህ ነው፤ እነርሱም ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች ይሆናሉ።”
34
ሙሴና አሮንም፥ የእስራኤልም አለቆች የቀዓትን ልጆች በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች ቈጠሩአቸው።
35
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ወደ አገልግሎት የገቡትን ሁሉ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቈጠሩአቸው፤
36
በየወገናቸውም ከእነርሱ የተቈጠሩት ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አምሳ ነበሩ።
37
እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ ሙሴና አሮን እንደ ቈጠሩአቸው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያገለግሉ ዘንድ የሚገቡት ሁሉ፥ የቀዓት ልጆች ቍጥር ይህ ነው።
38
የጌድሶንንም ልጆች በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች፥
39
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የገቡት ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቈጠሩአቸው።
40
ቍጥራቸውም በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች ሁለት ሺህ ስድስት መቶ አምሳ ነበር።
41
እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ የጌድሶን ልጆች ቍጥር ይህ ነው።
42
የሜራሪንም ልጆች ወገኖች በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች፥
43
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ወደ አገልግሎት የገቡት ሁሉ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቈጠሯቸው።
44
ቍጥራቸውም በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ነበረ።
45
እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው የሜራሪ ልጆች ወገኖች ቍጥር ይህ ነው።
46
በየወገናቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች ከሌዋውያን የተቈጠሩት ሁሉ፥ ሙሴና አሮን የእስራኤልም አለቆች የቈጠሩአቸው፥
47
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ሥራውን ለመሥራትና ዕቃውን ለመሸከም የገቡት ሁሉ፥ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥
48
ከእነርሱ የተቈጠሩት ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ነበሩ።
49
እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ እያንዳንዳቸው በየአገልግሎታቸውና በየሸክማቸው በሙሴ እጅ ተቈጠሩ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ በእርሱ ተቈጠሩ።
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 5 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36