bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Numbers 5
Numbers 5
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 4
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 6 →
1
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
2
“የእስራኤል ልጆች ለምጻሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ በሰውነቱ የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤
3
እኔ በመካከሉ የማድርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከወንድ እስከ ሴት ከሰፈሩ አውጡአቸው።”
4
የእስራኤልም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ከሰፈሩ አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ።
5
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
6
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወንድ ወይም ሴት ቸል ብለው ወይም ባለማወቅ ሰው ከሚሠራው ኀጢአት ሁሉ የሠሩት ቢኖር፥
7
ያች ሰውነት ብትናዘዝ፥ ያደረገችውንም ኀጢአት ሁሉ ብትናገር የወሰደውን ዓይነቱን ሁሉ ይመልስ። አምስተኛ እጅም ለባለ ገንዘቡ ይጨምር።
8
ነገር ግን ይመልስለት ዘንድ ሰውዬው ዘመድ ባይኖረው፥ ስለ በደል ለእግዚአብሔር የሚመልሰው ነገር ለካህኑ ይሁን፤ ይህም ስለ እርሱ ማስተስረያ ከሚደረግበት አውራ በግ ላይ ይጨመር።
9
የእስራኤልም ልጆች ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡአቸው የተቀደሱ ነገሮች ሁሉ የመጀመሪያው ለካህኑ ነው።
10
የተቀደሰ የሰው ነገር ሁሉ፥ ሰውም ለካህኑ የሚሰጠው ሁሉ ለእርሱ ይሁን።”
11
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
12
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ የማንኛውም ሰው ሚስት ከእርሱ ፈቀቅ ብትል፥ በእርሱም ላይ ብትበድል፥
13
ሌላም ሰው ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥ ብታመነዝር፥ ከባልዋም ዐይን ቢሸሸግ፥ እርስዋም ተሰውራ ብትረክስ፥
14
ምስክርም ባይኖርባት፥ በምንዝርም ባትያዝ፥ በባልዋም ላይ የቅንዐት መንፈስ ቢመጣበት፥ እርስዋም ስትረክስ ስለ ሚስቱ ቢቀና ወይም እርስዋ ሳትረክስ የቅንዐቱ መንፈስ ቢመጣበት፥ ስለ ሚስቱም ቢቀና፥
15
ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፤ የኢፍ መስፈሪያም ዐሥረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍርባን ስለ እርስዋ ያምጣ፤ የቅንዐት ቍርባን ነውና፥ ኀጢአትንም የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት።
16
“ካህኑም ያቀርባታል፤ በእግዚአብሔርም ፊት ያቆማታል፤
17
ካህኑም የተቀደሰ ውኃ በሸክላ ማሰሮ ይወስዳል፤ ካህኑም በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ካለው ትቢያ ወስዶ በውኃ ላይ ይረጨዋል፤
18
ካህኑም ሴቲቱን በእግዚአብሔር ፊት ያቆማታል፤ የሴቲቱንም ራስ ይገልጣል፤ በእጅዋም ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል ቍርባን፥ የቅንዐት ቍርባን ያኖራል፤ በካህኑም እጅ ርግማንን የሚያመጣው መራራ ውኃ ይሆናል።
19
ካህኑም ያምላታል፤ ሴቲቱንም እንዲህ ይላታል፦ ሌላ ወንድ አልተኛሽ፥ ባልሽንም አልተውሽ፥ ራስሽንም አላረከስሽ እንደ ሆነ፥ ርግማንን ከሚያመጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤
20
ነገር ግን ባልሽን ትተሽ ረክሰሽ እንደ ሆነ፥ ከባልሽም ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር ተኝቶ እንደ ሆነ፤
21
ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፤ ካህኑም ሴቲቱን እንዲህ ይበላት፦ እግዚአብሔር የተረገምሽ ያድርግሽ ጎንሽን ያረግፈው ዘንድ እግዚአብሔር ከሕዝብሽ መካከል ለይቶ ያጥፋሽ፤ ሆድሽን ይሰንጥቀው፤
22
ርግማንንም የሚያመጣ ይህ ውኃ ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ማኅፀንሽንም ይሰንጥቀው፤ ጎንሽም ይርገፍ። ሴቲቱም፦ ይሁን ይሁን ትላለች።
23
“ካህኑም እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ላይ ይጽፋቸዋል፤ በመርገሙም መራራ ውኃ ይደመስሳቸዋል፤
24
የመርገሙን መራራ ውኃ ለሴቲቱ ያጠጣታል፤ የርግማኑም ውኃ ወደ ሆድዋ ይገባል።
25
ካህኑም የቅንዐቱን መሥዋዕት ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፤ ያንም መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤
26
ካህኑም ከእህሉ ቍርባን አንድ እፍኝ ሙሉ ለመታሰቢያው ወስዶ በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል። ከዚያም በኋላ ለሴቲቱ ያን ውኃ ያጠጣታል።
27
ውኃውን ካጠጣት በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ ራስዋን አርክሳና ባልዋን ቸል ብላው ከሆነ፤ የመርገሙ መራራ ውኃ ወደ ሆድዋ ይገባል፤ ሆድዋንም ይሰነጥቀዋል፤ ጎኗም ይረግፋል፤ ሴቲቱም በሕዝብዋ መካከል ለመርገም ትሆናለች።
28
ራስዋን ያላረከሰች እንደ ሆነች፥ ያለ ነውርም እንደ ሆነች፥ ያነጻታል፤ ልጆችንም ትወልዳለች።
29
“በባልዋ ላይ ለበደለችና ራስዋን ላረከሰች ሴት የቅንዐት ሕግ ይህ ነው፤
30
በሰው ላይ የቅንዐት መንፈስ ቢመጣ፥ ስለ ሚስቱም ቢቀና፤ ሴቲቱን በእግዚአብሔር ፊት ያቆማታል፤
31
ካህኑም ይህን ሕግ ሁሉ ያደርግባታል። ሰውየውም ከኀጢአት ንጹሕ ይሆናል፤ ሴቲቱም ኀጢአቷን ትሸከማለች።”
← Chapter 4
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 6 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36