bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Micah 2
Micah 2
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 3 →
1
ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።
2
ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤ ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤ የሰውን ቤት፣ የባልንጀራን ርስት አታልለው ይወስዳሉ።
3
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት ላመጣ ዐቅጃለሁ፤ ከዚህም ለማምለጥ አትችሉም። ከእንግዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤ የመከራ ጊዜ ይሆናልና።
4
በዚያ ቀን ሰዎች ይሣለቁባችኋል፤ በሐዘን እንጕርጕሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኋል፤ ‘እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል፤ የወገኔ ርስት ተከፋፍሏል። ከእኔ ነጥቆ ወስዶ፣ ዕርሻዎቻችንን ላሸነፉን አከፋፈለ።’ ”
5
ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ ውስጥ፣ መሬት በዕጣ የሚያካፍል ማንም አይኖርም።
6
ነቢያቶቻቸው፣ “ትንቢት አትናገርብን፤ ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር፤ ውርደት አይደርስብንም” ይላሉ።
7
የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እንዲህ ሊባል ይገባልን? “ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? እንዲህ ያሉ ነገሮችንስ ያደርጋልን?” “መንገዱ ቀና ለሆነ፣ ቃሌ መልካም አያደርግምን?
8
በመጨረሻ በሕዝቤ ላይ ጠላት ሆናችሁ ተነሣችሁ፤ የጦርነት ሐሳብ ሳይኖራቸው፣ በሰላም ከሚያልፉ ሰዎች ላይ ማለፊያ መጐናጸፊያ ገፈፋችሁ።
9
ከሚወድዱት ቤታቸው፣ የሕዝቤን ሴቶች አስወጣችኋቸው፤ ክብሬን ከልጆቻቸው ለዘላለም ወሰዳችሁ።
10
ተነሡና ከዚያ ሂዱ፤ ይህ ማረፊያ ቦታችሁ አይደለምና፤ ምክንያቱም ረክሷል፤ ክፉኛም ተበላሽቷል።
11
ሐሰተኛና አታላይ ሰው መጥቶ፣ ‘ስለ ብዙ የወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ትንቢት እነግራችኋለሁ’ ቢል፣ ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ነቢይ ይሆናል።
12
“ያዕቆብ ሆይ፤ በርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤ የእስራኤልንም ትሩፍ በአንድነት አመጣለሁ፤ በጕረኖ ውስጥ እንዳሉ በጎች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ በአንድነት እሰበስባቸዋለሁ፤ ቦታውም በሕዝብ ይሞላል።
13
የሚሰብረው ወጥቶ በፊታቸው ይሄዳል፤ እነርሱም በሩን በመስበር ወጥተው ይሄዳሉ። እግዚአብሔር እየመራቸው፣ ንጉሣቸው ቀድሟቸው ይሄዳል።”
← Chapter 1
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 3 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7