bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Micah 3
Micah 3
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 4 →
1
ከዚያም እኔ እንዲህ አልሁ፤ “እናንት የያዕቆብ መሪዎች፤ እናንት የእስራኤል ቤት ገዦች ስሙ፤ ፍትሕን ማወቅ አይገባችሁምን?
2
መልካሙን ጠላችሁ፤ ክፉውንም ወደዳችሁ፤ የሕዝቤን ቈዳ ገፈፋችሁ፤ ሥጋቸውንም ከዐጥንቶቻቸው ለያችሁ፤
3
የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ፤ ቈዳቸውን ገፈፋችሁ፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሰባበራችሁ፤ በመጥበሻ እንደሚጠበስ፣ በድስት እንደሚቀቀል ሥጋ ቈራረጣችኋቸው።”
4
እነርሱም ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ እርሱ ግን አይመልስላቸውም፤ ካደረጉት ክፋት የተነሣ፣ በዚያ ጊዜ ፊቱን ከእነርሱ ይሰውራል።
5
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሕዝቤን የሚያስቱ ነቢያት፣ ሰው ሲያበላቸው፣ ‘ሰላም አለ’ ይላሉ፤ ሳያበላቸው ሲቀር ግን፣ ጦርነት ሊያውጁበት ይነሣሉ።
6
ስለዚህ ሌሊቱ ያለ ራእይ፣ ጨለማውም ያለ ንግርት ይመጣባችኋል፤ በነቢያት ላይ ፀሓይ ትጠልቅባቸዋለች፤ ቀኑም ይጨልምባቸዋል።
7
ባለ ራእዮች ያፍራሉ፤ ንግርተኞችም ይዋረዳሉ፤ ሁሉም ፊታቸውን ይሸፍናሉ፤ ከእግዚአብሔር መልስ የለምና።”
8
እኔ ግን፣ ለያዕቆብ በደሉን፣ ለእስራኤልም ኀጢአቱን እነግር ዘንድ፣ ኀይልን በእግዚአብሔር መንፈስ፣ ፍትሕና ብርታትም ተሞልቻለሁ።
9
እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣ እናንት የእስራኤል ቤት ገዦች፣ ፍትሕን የምትንቁ፣ ትክክለኛ የሆነውንም ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፤ ስሙ፤
10
ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ ኢየሩሳሌምን በክፋት የምትገነቡ፤ ስሙ።
11
መሪዎቿ በጕቦ ይፈርዳሉ፤ ካህናቷ ለዋጋ ሲሉ ያስተምራሉ፤ ነቢያቷም ለገንዘብ ሲሉ ይናገራሉ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ተደግፈውም፣ “ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይደርስብንም” ይላሉ።
12
ስለዚህ በእናንተ ምክንያት፣ ጽዮን እንደ ዕርሻ ትታረሳለች፣ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ የቤተ መቅደሱም ኰረብታ ዐረም የበቀለበት ጕብታ ይሆናል።
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7