bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Micah 5
Micah 5
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
← Chapter 4
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 6 →
1
አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤ ጭፍሮችሽን አሰልፊ ፤ ከበባ ተደርጎብናልና። የእስራኤልን ገዥ፣ ጕንጩን በበትር ይመቱታል።
2
“አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ አመጣጡ ከጥንት፣ ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣ የእስራኤል ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልኛል።”
3
ስለዚህ ወላዲቱ አምጣ እስክትገላገል ድረስ፣ እስራኤል ትተዋለች፤ የተቀሩት ወንድሞቹም፣ ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ።
4
በእግዚአብሔር ኀይል፣ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት፣ ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል። በዚያን ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣ ተደላድለው ይኖራሉ።
5
እርሱም ሰላማቸው ይሆናል። አሦራዊ ምድራችንን ሲወርር፣ ምሽጎቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣ ሰባት እረኞችን፣ እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።
6
የአሦርን ምድር በሰይፍ፣ የናምሩድን ምድር በተመዘዘ ሰይፍ ይገዛሉ ፤ አሦራዊው ምድራችንን ሲወርር፣ ዳር ድንበራችንን ሲደፍር፣ እርሱ ነጻ ያወጣናል።
7
የያዕቆብ ትሩፍ፣ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣ በሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ፣ ሰውን እንደማይጠብቅ፣ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ሰው ይሆናል።
8
በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣ የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣ በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣ እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣ የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል።
9
እጅህ በጠላቶችህ ላይ በድል አድራጊነት ከፍ ከፍ ትላለች፤ ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ።
10
“በዚያን ጊዜ” ይላል እግዚአብሔር ፤ “ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ ሠረገሎቻችሁን እደመስሳለሁ።
11
የምድራችሁን ከተሞች እደመስሳለሁ፤ ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ።
12
ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አታሟርቱም።
13
የተቀረጹ ምስሎቻችሁን፣ የማምለኪያ ዐምዶቻችሁንም ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ ለእጃችሁ ሥራ አትሰግዱም።
14
የአሼራ ምስልን ዐምድ ከመካከላችሁ እነቅላለሁ፤ ከተሞቻችሁንም እደመስሳለሁ።
15
ያልታዘዙኝን አሕዛብ፣ በቍጣና በመዓት እበቀላቸዋለሁ።”
← Chapter 4
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 6 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7