bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Proverbs 30
Proverbs 30
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 29
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 31 →
1
የማሳ አገር ሰው የያቄ ልጅ አጉር በጥሞና የተናገራቸው ንግግሮች የሚከተሉት ናቸው፦ “አምላክ ሆይ! ደክሜአለሁ፤ አምላክ ሆይ! ደክሜአለሁ፤ እንዴት ልቋቋመው እችላለሁ?
2
ከሰውነት ደረጃ ወጥቼ እንደ እንስሳ ሆኛለሁ፤ ሰው ሊኖረው የሚገባው ማስተዋል የለኝም።
3
ከቶ ጥበብን አልተማርኩም፤ ስለ እግዚአብሔር የማውቀው ምንም ነገር የለኝም።
4
ወደ ሰማይ ወጥቶ የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእጁ የጨበጠ፥ ውሃን በልብሱ የቋጠረ፥ የምድርን ዳርቻ ያጸና ማን ነው? የሰውዬው ስም ማነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? ታውቅ እንደሆን ንገረኝ፤
5
“እግዚአብሔር የሚናገረው ቃል ሁሉ እውነት ነው፤ ለሚታመኑበት ሁሉ ጋሻ ነው።
6
እርሱ ያላለውን ብሎአል ብትል ይገሥጽሃል፤ ሐሰተኛ መሆንህንም ይገልጣል።”
7
አምላክ ሆይ! ከመሞቴ በፊት የሚከተሉትን ሁለት ነገሮች እንዳትነሣኝ እለምንሃለሁ፦
8
ሰውን ከማታለልና ሐሰት ከመናገር ጠብቀኝ፤ የሚያስፈልገኝን ያኽል ምግብ ስጠኝ እንጂ ሀብታም ወይም ድኻ አታድርገኝ።
9
ብዙ ሀብት ቢኖረኝ “እግዚአብሔር ማን ነው?” ብዬ አንተን እስከ መካድ እደርሳለሁ፤ ድኻ ብሆን ደግሞ እሰርቅ ይሆናል፤ በዚህም ሁኔታ የአንተን የአምላኬን ስም አሰድባለሁ።
10
እንዳትረገምና መከራ ላይ እንዳትወድቅ አገልጋይን ባሳዳሪው ፊት አትንቀፈው።
11
አባቶቻቸውን የሚሰድቡ፥ እናቶቻቸውንም የማያመሰግኑ ሰዎች አሉ።
12
በጣም የረከሱ ሆነው ሳለ ንጹሕ የሆኑ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ።
13
በትዕቢት የተሞሉና ሰውን የሚንቁ ሰዎች አሉ።
14
ጥርሳቸው እንደ ሰይፍ፥ መንጋጋቸው እንደ ካራ የሆኑ ድኾችንና ችግረኞችን በግፍ የሚበዘብዙ ሰዎች አሉ።
15
አልቅት “ስጠኝ! ስጠኝ!” እያሉ የሚጮኹ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉአት፤ እንዲሁም ከቶ የማይጠግቡና በቃን የማይሉ ሦስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም አራት ናቸው፤
16
እነርሱም፦ “መቃብር፥ መኻን ሴት፥ ዝናብ የሚያስፈልገው ደረቅ ምድርና ከቊጥጥር ውጪ የሆነ የእሳት ቃጠሎ” ናቸው።
17
በአባቱ የሚያፌዝና እናቱ በምታረጅበት ጊዜ የሚንቃት ሰው የሸለቆ ቊራዎች ዐይኖቹን ጐጥጒጠው ያወጡታል፤ ጆፌ አሞራዎችም ይበሉታል።
18
ላስተውላቸው የማልችል እጅግ ምሥጢር የሆኑ ሦስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም አራት ናቸው።
19
እነርሱም፦ “በሰማይ የሚበር ንስር፥ በአለት ላይ የሚጐተት እባብ፥ በባሕር ላይ የሚጓዝ መርከብና ከሴት ጋር ፍቅር የያዘው ወንድ” ናቸው።
20
የማትታመን ሚስት ሁኔታም እንዲሁ ነው፤ እርስዋ በባልዋ ላይ ታመነዝርና ንጹሕ ሰው በመምሰል “ምንም በደል አልፈጸምኩም” ትላለች።
21
በሦስት ነገሮች ምክንያት ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ ልትታገሥም አትችልም፤ እንዲያውም አራት ናቸው፤
22
እነርሱም “ባሪያ ሲነግሥ፥ ቦዘኔ ሲጠግብ፥
23
የተጠላች ሴት ባል ስታገባና፥ ሴት ባሪያ እመቤትዋን ስትወርስ” የሚከሠቱ ሁኔታዎች ናቸው።
24
በዓለም ላይ በብልኅነታቸው የታወቁ አራት ትንንሽ ፍጥረቶች አሉ፤
25
ጒንዳኖች፦ ጒንዳኖች ደካሞች ናቸው፤ ነገር ግን በበጋ ጊዜ ምግባቸውን ያከማቻሉ።
26
ሽኮኮዎች፦ ሽኮኮዎች ብርቱዎች አይደሉም፤ ነገር ግን መኖሪያቸውን በአለቶች መካከል ይሠራሉ።
27
አንበጦች፦ አንበጦች ንጉሥ የላቸውም፤ ነገር ግን ሁሉም በሥነ ሥርዓት ይጓዛሉ።
28
እንሽላሊቶች፦ እንሽላሊቶች በእጅ ስለሚያዙ ቀላል ፍጥረቶች መስለው ቢታዩም፥ በቤተ መንግሥት እንኳ ሳይቀር በሁሉ ስፍራ ይገኛሉ።
29
አረማመዳቸው አስደሳች የሆነ ሦስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም አራት ናቸው፤
30
እነርሱም፥ በእንስሶች መካከል ብርቱ የሆኑና ከማንም ፊት የማይሸሹ አንበሶች፥
31
አውራ ፍየሎች፥ የሚንጐራደዱ አውራ ዶሮዎች፥ በሕዝቦቻቸው ፊት በክብር የሚታዩ ነገሥታት ናቸው።
32
ሞኝነትህ ትምክሕተኛ እንድትሆን ቢያደርግህና ክፉ ነገር ለማድረግ ብታቅድ፥ ቆም ብለህ አስብ።
33
ወተት ቢናጥ ቅቤ ያስገኛል፤ የሰው አፍንጫ ቢጠመዘዝ ይደማል፤ ቊጣ ቢነሣሣ ጠብን ያመጣል።
← Chapter 29
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 31 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31