bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Proverbs 4
Proverbs 4
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 5 →
1
ልጆቼ ሆይ! የአባታችሁን ምክር ስሙ፤ በጥንቃቄ አዳምጡ፤ ማስተዋልንም ታገኛላችሁ።
2
እኔ የማስተምራችሁ ትምህርት መልካም ስለ ሆነ ቸል አትበሉት።
3
እኔም አንድ ጊዜ ከአባቴ ጋር የምኖር ትንሽ ልጅ ነበርኩ፤ ለእናቴም አንድ ነበርኩ፤
4
አባቴም እንዲህ እያለ ያስተምረኝ ነበር፤ “ቃሌን በሙሉ ልብህ ያዘው፤ ትእዛዞቼንም ፈጽም፤ በሕይወትም ትኖራለህ።
5
ጥበብንና ማስተዋልን ለማግኘት ትጋ፤ እኔ የምልህን አትርሳ፤ ቸልም አትበለው።
6
ጥበብን አትተዋት፤ እርስዋም ትጠብቅሃለች፤ ውደዳት፤ እርስዋም ከአደጋ ሁሉ ትከላከልልሃለች።
7
ጥበብ ከሁሉ በላይ ስለ ሆነች እርስዋን ገንዘብ አድርግ፤ ያለህን ሁሉ ቢያስከፍልህም ማስተዋልን ለማግኘት ትጋ።
8
ጥበብን አክብራት፤ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አጥብቀህም ብትይዛት፥ ክብርን ትሰጥሃለች።
9
የክብርን አክሊል ታቀዳጅሃለች፤ የተዋበውንም ዘውድ ትሰጥሃለች።”
10
ልጄ ሆይ! አድምጠኝ፤ የምነግርህንም ስማ፤ ዕድሜህም ይረዝማል።
11
የጥበብን መንገድ አሳየሁህ፤ በቀና መንገድም መራሁህ።
12
በጥበብ ብትራመድ እርምጃህ አይታገድም፤ ብትሮጥም አትሰናከልም።
13
የተማርከው ትምህርት ሕይወትን ስለሚሰጥህ አጥብቀህ ያዘው፤ አትተወው፤ ደኅና አድርገህም ጠብቀው።
14
ክፉ ሰዎች በሚሄዱበት መንገድ አትሂድ፤ ምሳሌነታቸውንም አትከተል።
15
ከእርሱ ራቅ፤ በዚያም አትራመድ፤ ከእርሱ ርቀህ በራስህ መንገድ ሂድ።
16
ክፉ ነገር ካላደረጉ ዕረፍት አይኖራቸውም፤ በሰው ላይ ጒዳት ካላደረሱ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አጥተው ያድራሉ።
17
ዐመፅና ግፍ ለእነርሱ እንደ መብልና እንደ መጠጥ ናቸው።
18
የደጋግ ሰዎች መንገድ እንደ ንጋት ብርሃን ነው፤ የቀኑ ሙሉ ብርሃን እስኪሆን ድረስ ብርሃኑ እየጨመረ ይሄዳል።
19
የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ ይወድቃሉ፤ የመውደቂያቸው ምክንያት ምን እንደ ሆነ አያውቁም።
20
ልጄ ሆይ! እኔ የምለውን አተኲረህ ስማ፤ ንግግሬንም በጥሞና አድምጥ።
21
ከዐይንህ አታርቃቸው፤ በልብህም ውስጥ ጠብቃቸው።
22
እነርሱም ለሚያስተውሉአቸው ሕይወትን፥ ለመላ ሰውነትም ጤንነትን ይሰጣሉ።
23
ልብ የሕይወት ምንጭ ስለ ሆነ ልብህን ከሁሉ ነገር አስበልጠህ ጠብቀው።
24
ክፉ ንግግር ከአፍህ አይውጣ፤ ሐሰትንና ማታለልን ከአንተ አርቃቸው።
25
አመለካከትህ ቀጥተኛ ይሁን፤ ግራና ቀኝ ሳትል ወደፊት ተመልከት።
26
እግሮችህ በቀና መንገድ ላይ ይራመዱ። መንገድህም ሁሉ ይቃናልሃል።
27
አቅጣጫህን ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አታድርግ፤ ወደ ክፉ ነገር ከመሄድ እግርህን መልስ።
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 5 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31