bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Proverbs 7
Proverbs 7
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 6
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 8 →
1
ልጄ ሆይ! ቃሌን ጠብቅ፤ ትእዛዞቼንም በልብህ ውስጥ አኑር።
2
በሕይወት እንድትኖር ትእዛዞቼን ጠብቅ፤ የማስተምርህንም ሁሉ እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቅ፤
3
እንደ ጣትህ ቀለበት ጠብቃቸው፤ በልብህም ሰሌዳ ቅረጻቸው።
4
ጥበብን እንደ እኅትህ፥ ማስተዋልንም እንደ ቅርብ ወዳጅህ አድርገህ ቊጠራቸው።
5
እነርሱ ከአመንዝራ ሴት እንድትርቅና ከሌላ ሰው ሚስት አሳሳች ቃል እንድትጠበቅ ያደርጉሃል።
6
ከዕለታት አንድ ቀን በቤቴ መስኮት ወደ ውጪ እመለከት ነበር፤
7
ዕውቀት ከጐደላቸው ሰዎች መካከል ወጣቶችን ተመለከትኩ፤ ከእነርሱም መካከል አስተሳሰብ የጐደለው አንድ ወጣት አየሁ።
8
አንዲት ሴት በምትኖርበት ቤት አጠገብ ባለው መንገድ ማእዘን ያልፍ ነበር፤ ወደ ቤትዋም አቅጣጫ ይራመድ ነበር፤
9
ይህንንም ያደርግ የነበረው ወደ ማታ ጊዜ ጨለምለም ሲል ነበር፤
10
ከዚያም በኋላ ሴትዮዋ ወጣችና አገኘችው፤ አለባበስዋም ሴትኛ ዐዳሪ መሆኗን ያመለክት ነበር፤ ሰውንም የምታስትበት ዕቅድ ነበራት።
11
እርስዋ ደፋርና ኀፍረተቢስ ሴት ነበረች፤ በቤትዋ መቀመጥ ስለማያስደስታት ዘወትር ትዞራለች፤
12
በየማእዘኑ፥ በየመንገዱና በየገበያ ስፍራ እየቆመች ትጠባበቃለች።
13
ያንን ወጣት ዕቅፍ አድርጋ ሳመችው፤ ያለ ኀፍረት እንዲህ አለችው፦
14
“እኔ መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ የስእለቴን መባ አቅርቤአለሁ፤
15
ስለዚህ አንተን ለመቀበል ወጣሁ፤ በብርቱም ፈለግኹህ፤ እነሆም አገኘሁህ!
16
ከግብጽ አገር የመጣውን ጌጠኛ አንሶላ በአልጋዬ ላይ አንጥፌአለሁ።
17
ከርቤ አልሙንና ቀረፋ ከተባሉት ቅመሞች የተሠራ ሽቶ አርከፍክፌበታለሁ።
18
ና ሌሊቱን ሙሉ በፍቅር እንርካ፤ በመተቃቀፍም ደስ ይበለን!
19
ባሌ በቤት የለም፤ ወደ ሩቅ አገር ሄዶአል፤
20
ብዙ ገንዘብ ይዞ ስለ ሄደ እስከ ሁለት ሳምንት አይመለስም።”
21
በሚማርኩ ቃሎችዋ አግባባችው፤ በለዘበ አነጋገርዋም አታለለችው።
22
በሬ ወደሚታረድበት ስፍራ እንደሚነዳ፥ አጋዘንም ቸኲሎ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ፥ ወዲያውኑ እርስዋን ተከትሎ ሄደ፤
23
ፍላጻም ሆድ ዕቃውን እንደሚወጋው ዐይነት ሆነ፤ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ ወፍ መሰለ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕይወቱ በአደጋ ላይ ለመውደቅ መቃረቡን አላወቀም።
24
እንግዲህ ልጄ ሆይ! አድምጠኝ፤ የምልህንም በጥንቃቄ ስማ፤
25
እንደዚህ ዐይነትዋ ሴት ልብህን እንድትማርክ አታድርጋት፤ የእርስዋንም መንገድ በመከተል አትሳሳት።
26
እርስዋ ለብዙ ሰዎች የመጥፊያ ምክንያት ሆናለች፤ እጅግ ብዙ ሰዎች በእርስዋ ተማርከው ጠፍተዋል።
27
ወደ እርስዋ ቤት የሚወስደው መንገድ ወደ ሞትና ወደ መቃብር የሚያወርድ ጐዳና ነው።
← Chapter 6
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 8 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31