bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Genesis 18
Genesis 18
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 17
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 19 →
1
በቀትርም ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ ዛፍ ሥር ተገለጠለት።
2
ዐይኑንም በአነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤
3
እንዲህም አለ፥ “አቤቱ በፊትህስ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈው፤
4
ውኃ እናምጣላችሁ፤ እግራችሁንም እንጠባችሁ።
5
ከዛፉም ሥር ዕረፉ፤ እንጀራም እናምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያም በባሪያችሁ ዘንድ ከአረፋችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰባችሁት ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “እንዳልህ እንዲሁ አድርግ” አሉት።
6
አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሚስቱ ወደ ሣራ ፈጥኖ ገባና፥ “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ ለውሺ፤ እንጎቻም አድርጊ” አላት።
7
አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፤ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴናው ሰጠው፤ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኮለ።
8
እርጎና መዓር፥ ያን ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፤ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ያሳልፍላቸው ነበር፤ እነርሱም በሉ።
9
እርሱም፥ “ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?” አለው። እርሱም፥ “በድንኳኑ ውስጥ ናት” አለው።
10
እርሱም፥ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች” አለ።
11
ሣራም በድንኳኑ ደጃፍ በስተኋላው ቆማ ሳለች ይህን ሰማች። አብርሃምና ሣራም በዕድሜያቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር፤ በሴቶች የሚሆነውም ልማድ ከሣራ ተቋርጦ ነበር።
12
ሣራም ለብቻዋ በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፥ “እስከ ዛሬ ገና ነኝን? ጌታዬም ፈጽሞ ሽምግሎአል።”
13
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “ሣራን ለብቻዋ በልብዋ ምን አሳቃት? እስከ ዛሬ ገና ነኝን? በእውነትስ እወልዳለሁን? ጌታዬም አርጅትዋል እነሆ፥ እኔም አርጅቻለሁ ብላለችና።
14
በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች።”
15
ሣራም ስለ ፈራች “አልሳቅሁም” ብላ ካደች። እርሱም፥ “አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ” አላት።
16
እነዚያም ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ አቀኑ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ፤ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ።
17
እግዚአብሔርም አለ፥ “እኔ የማደርገውን ከወዳጄ አብርሃም አልሰውርም፤
18
አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና።
19
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
20
እግዚአብሔርም ለአብርሃም አለው፥ “የሰዶምና የገሞራ ጩኸት በእኔ ዘንድ በዛ፤ ኀጢአታቸውም እጅግ ከበደች፤
21
እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸቷ ይፈጽሙአት እንደ ሆነ አይ ዘንድ እወርዳለሁ፤ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ።”
22
ሰዎቹም ከዚያ በተመለሱ ጊዜ ወደ ሰዶም መጡ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።
23
አብርሃምም ቀረበ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ጻድቁ እንደ ኃጥኡ አይሁን።
24
አምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማዪቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?
25
አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
26
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “በሰዶም ከተማ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ከተማውን ሁሉ ስለ እነርሱ አድናለሁ።”
27
አብርሃምም መለሰ፤ አለም፥ “እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ከእግዚአብሔር ጋር እናገር ዘንድ አሁን ጀመርሁ፤
28
ከእነዚያ አምሳ ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማዪቱን ሁሉ በጐደሉት በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን?” እግዚአብሔርም፥ “ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ ስለ እነርሱ አላጠፋትም” አለው።
29
አብርሃምም አለው፥ “ከዚያ አርባ ቢገኙሳ?” እግዚአብሔርም፥ “ለአርባው ስል አላጠፋትም” አለው።
30
አብርሃምም እንደገና ነገሩን ደገመ፤ እንዲህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ሠላሳው አላጠፋትም” አለው።
31
ደግሞም፥ “እነሆ፥ ከጌታዬ ከእግዚአብሔር ጋር እነጋገር ዘንድ ባለሟልነትን ካገኘሁ ከዚያ ሃያ ቢገኙሳ?” አለው። እርሱም፥ “ስለ ሃያው አላጠፋትም” አለው።
32
አብርሃምም አለው፥ “አቤቱ እንደገና እናገር ዘንድ ፍቀድልኝ፤ ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ዐሥሩ አላጠፋትም” አለው።
33
እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ።
← Chapter 17
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 19 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50