bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Genesis 25
Genesis 25
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 24
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 26 →
1
አብርሃምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተባለች ሚስት አገባ።
2
እርስዋም ዘንበሪን፥ ዮቃጤንን፥ ሜዳንን፥ ዮብቅን፥ ምድያምንና ሴሂን ወለደችለት።
3
ዮቃጤንም ሶቤቅን፥ ቲማንንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች ራጉኤል፥ ንበከዝ፥ እስራኦምና ሎአም ናቸው።
4
የምድያምም ልጆች ጌፌር፥ ዔፋር፥ ሄኖኅ፥ አቢሮንና ቲያሮስ ናቸው። እነዚህም ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።
5
አብርሃምም በሕይወቱ ሳለ ገንዘቡን ሁሉ ለልጁ ለይስሐቅ ሰጠው፤
6
አብርሃምም ለቁባቶቹ ልጆች ሀብትን ሰጣቸው፤ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ምሥራቅ ሀገር ሰደዳቸው።
7
አብርሃምም የኖረበት የዕድሜው ዓመታት እነዚህ ናቸው፤ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ።
8
አብርሃምም መልካም ሽምግልናን ሸምግሎ፥ ዘመኑንም ፈጽሞ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተጨመረ።
9
ልጆቹ ይስሐቅና ይስማኤልም በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊው በሰዓር ልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።
10
ይህም አብርሃም ከኬጢ ልጆች የገዛው እርሻ ነው፤ አብርሃምንና ሚስቱን ሣራን በዚያ ቀበሩአቸው።
11
እንዲህም ሆነ፥ አብርሃምም ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር ልጁን ይስሐቅን ባረከው፤ ይስሐቅም ዐዘቅተ ራእይ ተብሎ በሚጠራው ምንጭ አጠገብ ኖረ።
12
የሣራ ባሪያ ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት የአብርሃም ልጅ የይስማኤል ትውልድ ይህ ነው፤
13
የይስማኤልም የልጆቹ ስም በየስማቸውና በየትውልዳቸው እንዲህ ነው።
14
የይስማኤል የበኵር ልጁ ናቡአት፥ ቄዳር፥ ነብዳኤል፥ መብሳን፥
15
ማሴሜ፥ ዱማ፥ ማሤን፥ ኩዳን፥ ቴማን፥ ኤያጤር፥ ናፌስ፥ ቄድን።
16
የይስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ይህ ነው፤ በየወገናቸውም ዐሥራ ሁለት አለቆች ናቸው።
17
እርሱም ከኤውላጥ አንሥቶ በግብፅ ፊት ለፊት እስከምትገኝ እስከ ሴይር ባለው ሀገር ኖረ፤ ወደ አሦርዮንም ደረሰ፤ እንዲህም ከወንድሞቹ ሁሉ ፊት ተቀመጠ።
18
ይስማኤልም የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው ፤ ሸምግሎ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተጨመረ።
19
የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ትውልድም ይህ ነው፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፥
20
ይስሐቅም ሚስት ትሆነው ዘንድ የሶርያዊውን የላባን እኅት፥ የሶርያዊውን የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ከሁለቱ ከሶርያ ወንዞች መካከል በወሰዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።
21
ይስሐቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግዚአብሔር ለመነ፤ መካን ነበረችና፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብቃም ፀነሰች።
22
ልጆችዋም በሆድዋ ውስጥ ይንቀሳቀሱ ነበር ፤ እርስዋም፥ “እንዲህ እሆን ዘንድ ካለኝ ይህ ለእኔ ምኔ ነው?” አለች። ወደ እግዚአብሔርም ትለምን ዘንድ ሄደች።
23
እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
24
የምትወልድበትም ወራት ተፈጸመ፤ በማኅፀንዋም መንታ ነበሩ።
25
የበኵር ልጅዋም ወጣ፤ እንደ ጽጌረዳም ቀይ ነበረ፤ ሁለንተናውም ጠጕራም ነበር፤ ስሙንም ዔሳው ብላ ጠራችው።
26
ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙንም ያዕቆብ ብላ ጠራችው። ርብቃ ዔሳውንና ያዕቆብን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
27
ብላቴኖቹም አደጉ፤ ጐለመሱም፤ ዔሳውም አደን የሚያውቅ የበረሃ ሰው ሆነ፤ ያዕቆብ ግን ጭምት ሰው ነበረ፤ በቤትም ይቀመጥ ነበር።
28
ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበር፤ እርሱ ከአደነው ይበላ ነበርና። ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበረች።
29
ለያዕቆብም የምስር ንፍሮ ቀቀለችለት፤ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ፤
30
ዔሳውም ያዕቆብን፥ “ከምስር ንፍሮህ አብላኝ፤ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና” አለው፤ ስለዚህም ስሙ ኤዶም ተባለ።
31
ያዕቆብም ዔሳውን፥ “ዛሬ ብኵርናህን ስጠኝ” አለው።
32
ዔሳውም፥ “እነሆ፥ እኔ ልሞት ነኝ፤ ይህች ብኵርና ለምኔ ናት?” አለ።
33
ያዕቆብም፥ “ብኵርናህን ትሰጠኝ ዘንድ እስኪ ዛሬ ማልልኝ” አለው። ዔሳውም ማለለት፤ ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ።
34
ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራና የምስር ንፍሮ ሰጠው፤ በላ፥ ጠጣ፥ ተነሥቶም ሄደ፤ ዔሳውም ብኵርናውን አቃለላት።
← Chapter 24
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 26 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50