bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Genesis 42
Genesis 42
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 41
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 43 →
1
ያዕቆብም በግብፅ የሚሸመት እህል እንዳለ ሰማ፤ ልጆቹንም፥ “ለምን ትተክዛላችሁ?” አላቸው።
2
እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ እህል በግብፅ እንዳለ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚያ ውረዱ፤ እንድንድንና በራብ እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን።”
3
የዮሴፍም ዐሥሩ ወንድሞቹ እህልን ከግብፅ ይሸምቱ ዘንድ ወረዱ፤
4
የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፥ “ምናልባት ክፉ እንዳያገኘው” ብሎአልና።
5
የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡት ጋር ገቡ፤ በከነዓን ሀገር ራብ ነበርና።
6
ዮሴፍም በግብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግንባራቸው ሰገዱለት።
7
ዮሴፍም ወንድሞቹን በአያቸው ጊዜ ዐወቃቸው፤ እንደማያውቃቸውም ሆነ፤ ክፉ ቃልንም ተናገራቸው፥ “እናንተ ከወዴት መጣችሁ?” አላቸው። እነርሱም፥ “ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን” አሉት።
8
ዮሴፍም ወንድሞቹን ዐወቃቸው፤ እነርሱ ግን አላወቁትም፤ ዮሴፍም አይቶት የነበረውን ሕልም ዐሰበ።
9
እንዲህም አላቸው፥ “እናንተ ሰላዮች ናችሁ ፤ የሀገሩን ሁኔታ ልታዩ መጥታችኋል።”
10
እነርሱም አሉት፥ “ጌታ ሆይ፥ አይደለም፤ ባሪያዎችህስ ስንዴ ሊገዙ መጥተዋል፤
11
እኛ ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የሰላም ሰዎች ነን፤ ባሪያዎችህስ ሰላዮች አይደሉም።”
12
እርሱም አላቸው፥ “አይደለም፤ ነገር ግን እናንተ ሰላዮች ናችሁ፤ የሀገሩንም ሁኔታ ልታዩ መጥታችኋል።”
13
እነርሱም አሉ፥ “ባሪያዎችህ በከነዓን ምድር የምንኖር ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ ታናሹም እነሆ ዛሬ ከአባታችን ጋር ነው፤ ሌላውም ሞቶአል።”
14
ዮሴፍም አላቸው፥ “እናንተ ሰላዮች ናችሁ ብዬ የተናገርሁአችሁም ይህ ነው፤ በዚህ ትታወቃላችሁ፤
15
ታናሽ ወንድማችሁን ከአላመጣችሁ በቀር ‘የፈርዖንን ሕይወት!’ ከዚህ አትወጡም።
16
ወንድማችሁን ያመጣ ዘንድ ከእናንተ አንዱን ላኩ፤ እናንተ ግን እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ወይም ከአልሆነ ነገራችሁ እስኪታወቅ ድረስ ከዚህ ተቀመጡ፤ ይህ ከአልሆነ ‘የፈርዖንን ሕይወት!’ ሰላዮች ናችሁ።”
17
ሦስት ቀን ያህልም በግዞት ቤት ጨመራቸው።
18
በሦስተኛው ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔርን እፈራለሁና።
19
እናንተ ሰላማውያን ከሆናችሁ ከእናንተ አንዱ ወንድማችሁ በግዞት ቤት ይታሰር፤ እናንተ ግን ሂዱ፤ የሸመታችሁትን እህልም ውሰዱ፤
20
ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገራችሁ የታመነ ይሆናልና፤ ይህ ከአልሆነ ግን ትሞታላችሁ።” እንዲህም አደረጉ።
21
እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፥ “በእውነት ወንድማችንን በድለናል፤ እኛን በመማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና፤ ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።”
22
ሮቤልም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ብላቴናውን አትበድሉ ብዬአችሁ አልነበረምን? እኔንም አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህ እነሆ፥ አሁን ደሙ ይፈላለጋችኋል።”
23
እነርሱም ዮሴፍ ነገራቸውን እንደሚሰማባቸው አላወቁም፤ በመካከላቸው አስተርጓሚ ነበርና።
24
ዮሴፍም ከእነርሱ ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ደግሞም ወደ እነርሱ ተመልሶ ተናገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ወስዶ በፊታቸው አሰረው።
25
ዮሴፍም ዓይበታቸውን እህል ይሞሉት ዘንድ አዘዘ፤ የየራሳቸውንም ብር በየዓይበታቸው ይመልሱት ዘንድ፥ ደግሞም የመንገድ ስንቅ ይሰጡአቸው ዘንድ አዘዘ። እንዲህም አደረጉ።
26
እነርሱም እህሉን በአህዮቻቸው ላይ ጫኑ፤ ከዚያም ተነሥተው ሄዱ።
27
ከእነርሱም አንዱ በአደሩበት ስፍራ ለአህዮቹ ገፈራን ይሰጥ ዘንድ ዓይበቱን ፈታ፤ ብሩንም በዓይበቱ አፍ ተቋጥሮ አገኘ።
28
ለወንድሞቹም፥ “ብሬ ተመለሰችልኝ፤ እርስዋም በዓይበቴ አፍ እነኋት” አላቸው። ልባቸውም ደነገጠ፤ እየታወኩም እርስ በርሳቸው ተባባሉ፥ “እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ምንድን ነው?”
29
ወደ አባታቸውም ወደ ያዕቆብ ወደ ከነዓን ምድር መጡ፤ የደረሰባቸውንም ነገር ሁሉ እንዲህ ብለው አወሩ፦
30
“የሀገሩ ጌታ የሆነው ሰው በክፉ ንግግር ተናገረን፤ የምድሪቱም ሰላዮች እንደሆን አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባን።”
31
እኛም እንዲህ አልነው፥ “ሰላማውያን ሰዎች ነን እንጂ ሰላዮች አይደለንም፤
32
እኛ የአባታችን ልጆች ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ ሞቶአል፤ ታናሹም በከነዓን ምድር ዛሬ ከአባታችን ጋር አለ።
33
የሀገሩም ጌታ ያ ሰው እንዲህ አለን፦ ‘ሰላማውያን ሰዎች ከሆናችሁ በዚህ ዐውቃለሁ፤ አንደኛውን ወንድማችሁን ከእኔ ጋር ተዉት፤ ለቤታችሁም የሸመታችሁትን እህል ይዛችሁ ሂዱ፤
34
ታናሹንም ወንድማችሁን አምጡልኝ፤ ሰላማውያን እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁንም በዚህ ዐውቀዋለሁ፤ ወንድማችሁንም እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በሀገራችን ትነግዳላችሁ።’ ”
35
እንዲህም ሆነ፤ ዓይበታቸውን በፈቱ ጊዜ እነሆ፥ ከእነርሱ እያንዳንዳቸው ብራቸውን በዓይበታቸው ተቋጥሮ አገኙት፤ እነርሱም አባታቸውም የተቋጠረ ብራቸውን አይተው ፈሩ።
36
አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፥ “ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።”
37
ሮቤልም አባቱን አለው፥ “ወደ አንተ መልሼ ያላመጣሁት እንደሆነ ሁለቱን ልጆችን ግደል፤ ልጅህን በእጄ ስጠኝ፤ እኔም ወደ አንተ እመልሰዋለሁ።”
38
እርሱም አለ፥ “ልጄ ከእናንተ ጋር አይወርድም፤ ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና፤ በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፉ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።”
← Chapter 41
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 43 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50