bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Genesis 4
Genesis 4
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 5 →
1
አዳምም ሚስቱን ሔዋንን ዐወቃት፤ ፀነሰችም፤ ቃየልንም ወለደችው።
2
እርስዋም “ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ” አለች። ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደችው። አቤልም በግ ጠባቂ ሆነ፤ ቃየልም ምድርን የሚያርስ ሆነ።
3
ከብዙ ቀን በኋላም እንዲህ ሆነ፤ ቃየል ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤
4
አቤልም ደግሞ ከበጎቹ መጀመሪያ የተወለደውንና ከሰቡት አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤
5
ወደ ቃየልና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም። ቃየልንም እጅግ አሳዘነው፤ ፊቱም ጠቈረ።
6
እግዚአብሔር አምላክም ቃየልን አለው፥ “ለምን ታዝናለህ? ለምንስ ፊትህ ጠቈረ?
7
በእውነት ያመጣህልኝ አይደለም፤ አግባብስ በእውነት ታመጣልኝ ዘንድ ነበር። በደልህ፤ እንግዲህ ዝም በል፤ የወንድምህ መመለሻው ወደ አንተ ነው፤ አንተም ትሰለጥንበታለህ።”
8
ቃየልም ወንድሙን አቤልን፥ “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፤ ገደለውም።
9
እግዚአብሔርም ቃየልን አለው፥ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” ቃየልም አለ፥ “አላውቅም፤ በውኑ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን?”
10
እግዚአብሔርም አለው፥ “ቃየል! ምን አደረግህ? የወንድምህ የአቤል የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮሃል።
11
አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።
12
ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኀይልዋን አትሰጥህም፤ በምድር ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ።”
13
ቃየልም እግዚአብሔርን አለው፥ “ኀጢአቴ ይቅር የማትባል ታላቅ ናትን?
14
እነሆ፥ ዛሬ ከምድር ፊት ከአሳደድኸኝ፥ ከፊትህ እሰወራለሁ፤ በምድርም ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ፤ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል።”
15
እግዚአብሔርም አለው፥ “እንዲህ አይደለም፤ እንግዲህ ቃየልን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልበታል።” እግዚአብሔርም ቃየልን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት።
16
ቃየልም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፤ በኤዶም አንጻር ባለችው ኖድ በምትባለው ምድርም ኖረ።
17
ቃየልም ሚስቱን ዐወቃት፤ ፀነስችም፤ ሄኖሕንም ወለደች። ከተማም ሠራ፤ የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም “ሄኖሕ” አላት።
18
ሄኖሕም ጋይዳድን ወለደ፤ ጋይዳድም ሜኤልን ወለደ፤ ሜኤልም ማቱሳኤልን ወለደ፤ ማቱሳኤልም ላሜሕን ወለደ።
19
ላሜሕም ለራሱ ሁለት ሚስቶችን አገባ፤ የአንዲቱ ስም ዓዳ፥ የሁለተኛይቱ ስም ሴላ ነበር።
20
ዓዳም ዮቤልን ወለደች፤ እርሱም በድንኳን የሚቀመጡት የዘላኖች አባት ነበረ።
21
የወንድሙም ስም ኢዮቤል ነበር፤ እርሱም በገናንና መሰንቆን አስተማረ።
22
ሴላም ደግሞ ቶቤልን ወለደች። እርሱም ናስና ብረትን የሚሠራ ሆነ። የእኅቱም ስም ኖሄም ነበረ።
23
ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው፥ “እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገሬንም አድምጡ፤ እኔ ጐልማሳውን ስለ መቍሰሌ፤ ብላቴናውንም ስለ መወጋቴ ገድየዋለሁና፤
24
ቃየልን ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል፤ ላሜሕን ግን ሰባ ጊዜ ሰባት።”
25
አዳምም ዳግመኛ ሚስቱን ዐወቃት፤ ፀነሰችም፤ ወንድ ልጅንም ወለደች። ስሙንም ቃየል በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኛል ስትል ሴት አለችው።
26
ሴትም ወንድ ልጅ ወለደ። ስሙንም ሄኖስ አለው፤ እርሱም የእግዚአብሔርን ስም መጥራት የጀመረ ነው።
← Chapter 3
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 5 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50