bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Genesis 8
Genesis 8
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 7
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 9 →
1
እግዚአብሔርም ኖኅን፥ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዊቱን ሁሉ፥ እንስሳውንም ሁሉ፥ አዕዋፍንም ሁሉ፥ የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግዚአብሔርም በምድር ላይ ነፋስን አመጣ፤ ውኃውም ጐደለ፤
2
የቀላዩም ምንጮች፥ የሰማይም መስኮቶች ተደፈኑ፤ ዝናብም ከሰማይ ተከለከለ፤
3
ውኃውም ከምድር ላይ እያደር እየቀለለ ይሄድ ጀመረ፤ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኃው ጐደለ።
4
መርከቢቱም በሰባተኛው ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች።
5
ውኃውም እስከ ዐሥረኛው ወር ድረስ ይጐድል ነበር፤ በዐሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የተራሮቹ ራሶች ተገለጡ።
6
ከአርባ ቀን በኋላም ኖኅ የሠራውን የመርከቢቱን መስኮት ከፈተ፤
7
ከምድርም ላይ ውኃዉ ጐድሎ እንደሆነ ያይ ዘንድ ቁራውን ላከው፤ እርሱም ሄደ፤ ነገር ግን ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ አልተመለሰም።
8
ርግብንም ውኃው ከምድር ፊት ጐድሎ እንደ ሆነ እንድታይ ከእርሱ በኋላ ላካት።
9
ነገር ግን ርግብ እግርዋን የምታሳርፍበት ስፍራ አላገኘችም፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ተመለሰች፤ ውኃው በምድር ላይ ሁሉ ነበረና፤ እጁን ዘረጋና ተቀበላት፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ውስጥ አገባት።
10
ከዚያም በኋላ ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግብን እንደገና ከመርከብ ላካት።
11
ርግብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሰች፤ በአፍዋም እነሆ፥ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከምድር ላይ ውኃው እንደ ጐደለ ዐወቀ።
12
ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግብን ላካት፤ ዳግመኛም ወደ እርሱ አልተመለሰችም።
13
በኖኅ ዕድሜ በስድስት መቶ አንድ ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውኃው ከምድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅም የሠራትን የመርከቢቱን ክዳን አነሣ፤ እነሆም፥ ውኃው ከምድር ፊት እንደ ደረቀ አየ።
14
በሁለተኛውም ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን ምድር ደረቀች።
15
እግዚአብሔርም ለኖኅ እንዲህ ብሎ ነገረው፤
16
“አንተ ሚስትህንና ልጆችህን፥ የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ከመርከብ ውጣ።
17
ከአንተ ጋር ያሉትን አራዊት ሁሉ፥ ሥጋ ያላቸውን ሁሉ፥ ወፎችንና እንስሶችን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ከአንተ ጋር አውጣቸው፤ በምድርም ላይ ብዙ፤ ተባዙ። ምድርንም ሙሉአት።”
18
ኖኅም ሚስቱን፥ ልጆቹንና የልጆቹንም ሚስቶች ከእርሱ ጋር ይዞ ወጣ፤
19
አራዊት ሁሉ፥ እንስሳም ሁሉ፥ ወፎችም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚርመሰመሰው ሁሉ በየወገናቸው ከመርከብ ወጡ።
20
ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያዉን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ፥ ከንጹሓን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፤ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።
21
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
22
በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።”
← Chapter 7
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 43
Chapter 44
Chapter 45
Chapter 46
Chapter 47
Chapter 48
Chapter 49
Chapter 50
Chapter 9 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50