bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Job 29
Job 29
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 28
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 30 →
1
ኢዮብም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2
“የአሁኑ ኑሮዬ ቀድሞ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ እንደ ነበረው ጊዜ ቢሆንልኝ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር!
3
ያን ጊዜ በጨለማ ውስጥ ስሄድ፥ እግዚአብሔር መብራቱን እያበራልኝ በብርሃን እራመድ ነበር።
4
ምነው የእግዚአብሔር ረድኤት ቤቴን ይጠብቅ እንደ ነበረበት እንደ ወጣትነቴ ጊዜ በሆንኩ!
5
ሁሉን የሚችል አምላክ ገና ስላልተለየኝ፥ ልጆቼ ሁሉ በዙሪያዬ ነበሩ።
6
እግሮቼ እንኳ በወተት እስኪታጠቡ ድረስ ብዙ ወተት አገኝ ነበር። የወይራ ዛፎቼም በጭንጫ መሬት ላይ እንኳ ተተክለው እንደ ጐርፍ የሚወርድ ብዙ ዘይት ይሰጡኝ ነበር።
7
ወደ ከተማም አደባባይ እየሄድኩ በሸንጎ እቀመጥ በነበረ ጊዜ፥
8
ወጣቶች እኔን ሲያዩ በአክብሮት ከፊቴ ገለል ይሉ ነበር፤ ሽማግሌዎችም ስለ እኔ ክብር ከተቀመጡበት ይነሡ ነበር።
9
ሲነጋገሩ የነበሩ የሕዝብ መሪዎችም እኔን ሲያዩ እጆቻቸውን በአፋቸው ላይ አድርገው ጸጥ ይሉ ነበር።
10
የአገር መኳንንትም እኔ ባለሁበት ጸጥ ይሉ ነበር፤ ምላሳቸው ተሳስሮ መናገር ያቅታቸው ነበር።
11
“የሰማኝ ሁሉ አሞገሰኝ፤ ያየኝ ሁሉ አመሰገነኝ።
12
ይህም የሆነው የድኾችን ጩኸት ሰምቼ እታደጋቸውና፥ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውንም ልጆች እረዳቸው ስለ ነበረ ነው።
13
ለሞት የተቃረቡትን ሰዎች ስለምረዳ መረቁኝ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ስለምረዳቸው በደስታ ይዘምሩ ነበር።
14
ጽድቅን እንደ ልብስ ለበስኳት፤ ትክክለኛ ፍርድንም እንደ ካባ ደረብኳት፤ እንደ ቆብም ደፋኋት።
15
ለዕውሮች ዐይን፥ ለአንካሶችም እግር ነበርኩ።
16
ለድኾች አባት፥ ለማላውቃቸውም ሰዎች ጠበቃ ነበርኩ።
17
የግፈኛውን መንጋጋ ሰበርኩ፤ ነጥቆ የወሰደውንም ከአፉ አስጣልኩ።
18
“ ‘ዕድሜዬ እንደ አሸዋ በዝቶ፥ በቤቴ እንዳለሁ በክብር እሞታለሁ’ ብዬ ነበር።
19
ሥሮቹ ዘወትር ውሃ እንደሚያገኙና ቅርንጫፎቹም በጠል እንደሚርሱ ዛፍ ነበርኩ።
20
ሁልጊዜ እንደ ተከበርኩ እኖር ነበር ኀይሌም ዘወትር ይታደስ ነበር።
21
ሰዎች እኔን በማዳመጥ ጸጥ ይሉ ነበር፤ ምክሬንም ለመስማት በዝምታ ያዳምጡ ነበር።
22
ንግግሬ ያረካቸው ስለ ነበር፥ ከእኔ ንግግር በኋላ የሚናገር ሰው አልነበረም።
23
ገበሬ የበልግ ዝናብ ለማግኘት እንደሚመኝ፤ እነርሱም የኔን ንግግር ለመስማት አፋቸውን ከፍተው ይጠባበቁ ነበር።
24
ፈገግ ስልላቸው ተዝናኑ፤ ፊቴ ሲበራ የተቋጠረ ፊታቸው ተፍታታ።
25
እኔ እንደ ፈለግኹት አስተዳድራቸው ነበር፤ ሠራዊቱንም እንደሚመራ ንጉሥ እመራቸው ነበር፤ በሚያዝኑበትም ጊዜ አጽናናቸው ነበር።”
← Chapter 28
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 30 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42