bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Job 32
Job 32
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 31
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 33 →
1
ኢዮብ “እኔ ጻድቅ ሰው ነኝ” ብሎ በሐሳቡ ስለጸና፥ ሦስቱ ሰዎች ንግግራቸውን አቆሙ።
2
የራም ቤተሰብ የነበረው ቡዛዊው የባራኬል ልጅ ኤሊሁ ኢዮብ ራሱን ከእግዚአብሔር አብልጦ ጻድቅ ስላደረገ ተቈጣ።
3
በኢዮብ ላይ የሚያስፈርድ በቂ መልስ ባለመስጠታቸው፥ ኤሊሁ በሦስቱ ጓደኞቹም ላይ ተቈጥቶ ነበር።
4
ኤሊሁ በዕድሜ ከሌሎቹ ያነሰ በመሆኑ ሁሉም ተናግረው እስከሚጨርሱ ድረስ በተራው ከኢዮብ ጋር ለመናገር ይጠባበቅ ነበር።
5
ሦስቱ ሰዎች ለኢዮብ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት አለመቻላቸውን በማየቱ እጅግ ተቈጣ።
6
ቡዛዊው የባራኪ ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ በዕድሜዬ ከእናንተ ያነስኩ በመሆኔና እናንተም አዛውንት በመሆናችሁ፥ ኀፍረትና ፍርሀት ተሰምቶኝ ሐሳቤን ሳልገልጥ እስከ አሁን ቈይቼ ነበር።
7
‘ሽማግሌዎች በቅድሚያ ይናገሩ፤ በረጅም ዕድሜ ያገኙትን ጥበብ ያስተምሩ’ ብዬ ነበር።
8
ነገር ግን በሰው ዐድሮ ጥበብን የሚሰጥ የልዑል እግዚአብሔር መንፈስ ነው።
9
ሰዎችን ጠቢባን የሚያደርጋቸው ሽምግልና አይደለም፤ ትክክለኛውንም ነገር ለማስተዋል የሚረዳቸው የዕድሜ ብዛት አይደለም።
10
ስለዚህ እኔም ሐሳቤን ልግለጥላችሁ፤ እናንተም በጥሞና አድምጡኝ።
11
“እናንተ የምታቀርቡትን ምክንያት እጠባበቅ ነበር። ሐሳባችሁን ግልጥ ለማድረግ ቃላት በመምረጥ፥ የምትናገሩትንም አዳምጥ ነበር።
12
በጥንቃቄ አደመጥኳችሁ፤ ሆኖም፥ ማንም ኢዮብን ለማስተባበል የቻለ የለም፤ ከእናንተም መካከል ለእርሱ ንግግር አጥጋቢ መልስ የሰጠ የለም።
13
ለኢዮብ ተገቢ መልስ ሊሰጠው የሚችል እግዚአብሔር እንጂ ሰው ስላልሆነ፥ እናንተ ጥበብን አግኝተናል ብላችሁ በከንቱ አትመኩ።
14
ኢዮብ የተከራከረው ከእናንተ ጋር እንጂ ከእኔ ጋር አልነበረም፤ እኔም በእናንተ አነጋገር ዐይነት አልመልስለትም።
15
“እነርሱም ደንግጠው የሚናገሩት ነገር ስላልነበራቸው ምንም መናገር አልቻሉም።
16
እነሆ! እነርሱ የሚናገሩትን አጥተው ዝም ብለው ቆመዋል፤ ታዲያ፥ እነርሱ ጸጥ ቢሉ፥ እኔም በትዕግሥት መጠባበቅ ይገባኛልን?
17
አይሆንም! እኔም የበኩሌን መልስ እሰጣለሁ፤ አስተያየቴንም እገልጣለሁ።
18
ብዙ የምናገረው ነገር ስላለኝ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ዝም ማለት አልችልም።
19
ሆዴ ሊፈነዳ እንደ ተቃረበ እንደ አዲስ የወይን አቊማዳ ሆዴ ተነፍቶአል።
20
ተናግሬ ይውጣልኝ፤ በአንደበቴ መልስ መስጠት አለብኝ።
21
በዚህ ጉዳይ ለማንም አላደላም፤ ማንንም አላቆላምጥም።
22
እኔ ሰውን ማቈላመጥ አይሆንልኝም፤ ይህንንም ባደርግ ፈጣሪዬ በፍጥነት ይቀጣኝ ነበር።”
← Chapter 31
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 33 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42