bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Job 3
Job 3
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 4 →
1
ከዚህ በኋላ ኢዮብ መናገር ጀመረ፤ የተወለደበትን ቀን እንዲህ ሲል ረገመ፦
2
“የተፀነስኩበት ሌሊት፥ የተወለድኩበትም ቀን የተረገመ ይሁን!
4
ያ ቀን ወደ ጨለማ ይለወጥ፤ የሰማይ አምላክ አያስበው፤ ብርሃን ከቶ አይታይበት።
5
በጭጋግና በድቅድቅ ጨለማ የተሸፈነ ይሁን፤ ደመና ረቦበት ጨለማ ብርሃኑን ይዋጠው፤
6
ያን ሌሊት ድቅድቅ ጨለማ ይሸፍነው፤ ከዓመቱ ቀኖች ጋር አይቈጠር፤ ከወሮቹም ውስጥ ገብቶ አይታሰብ።
7
ያ ሌሊት ባዶ ይሁን፤ የደስታም ድምፅ አይሰማበት።
8
ሌዋታንን መቀስቀስ የሚችሉና ቀኖችን የሚረግሙ አስማተኞች ያን ቀን ይርገሙት።
9
የዚያ ሌሊት አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፤ የብርሃን ተስፋ አይገኝበት፤ የንጋትም ጮራ አይፈንጥቅበት።
10
ችግርን ከዐይኖቼ ለመሸሸግ የማሕፀን በሮችን በእኔ ላይ ስላልዘጋ ያ ቀን የተረገመ ይሁን።
11
“ምነው በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ ውሃ ሆኜ በቀረሁ! ከማሕፀን ስወጣስ ለምን አልጠፋሁም?
12
ጒልበቶች እኔን ለመቀበል፥ ጡቶችም እኔን ያጠቡ ዘንድ ለምን ተገኙ?
13
አሁን በሰላም በተጋደምኩ፥ አንቀላፍቼም ዕረፍት ባገኘሁ ነበር።
14
አሁን ፈርሰው የሚታዩትን ለራሳቸው ከገነቡት የምድር ነገሥታትና አማካሪዎች ጋር አንቀላፍቼ ዕረፍት ባገኘሁ ነበር።
15
ቤቶቻቸውን በወርቅና በብር ከሞሉ መሳፍንት ጋር አብሬ በተኛሁ ነበር፤
16
ወይስ ለምን በመሬት ውስጥ እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ የቀንን ብርሃን ፈጽሞ እንዳላየ ሕፃን አልሆንኩም?
17
በዚያ ክፉዎች አስቸጋሪነታቸው ይቀራል፤ በአድካሚ ሥራም የኖሩ ያርፋሉ።
18
እስረኞች እንኳ ሰላም ያገኛሉ፤ የአሠሪዎቻቸውን የቊጣ ድምፅ ከመስማት ይድናሉ።
19
ታናናሽና ታላላቅ ሰዎች በአንድነት ይገኛሉ፤ ባሪያዎችም በዚያ ከጌቶቻቸው ነጻ ይወጣሉ።
20
“በጭንቀት ላይ ላሉ ብርሃን፥ ኑሮአቸው በመራራ ሐዘን ለተመላ ሕይወት የሚሰጣቸው ለምንድነው?
21
ሞትን ለሚናፍቁና፥ ከተደበቀ ሀብት ይልቅ ፈልገው የማያገኙት ሕይወት የሚሰጣቸው ለምንድን ነው?
22
ወደ መቃብር ሲደርሱ ደስታ ለሚሰማቸው ሕይወት የሚሰጣቸው ለምንድን ነው?
23
መንገዱ ለተሰወረበትና እግዚአብሔር ለዘጋበት ሰው ብርሃን የሚሰጠው ለምንድን ነው?
24
በምግብ ፈንታ እቃትታለሁ፤ ጩኸቴም እንደ ፈሳሽ ውሃ ነው።
25
የፈራሁት ነገር መጥቶብኛል፤ የደነገጥሁበትም ነገር ደርሶብኛል።
26
በውስጤ ሁከት ብቻ ስላለ፥ ሰላም፥ ጸጥታና ዕረፍት የለኝም።”
← Chapter 2
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 4 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42