bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Job 11
Job 11
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 10
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 12 →
1
አሜናዊው ሶፋር መለሰ፥ እንዲህም አለ፦
2
“ብዙ እንደምትናገር እንዲሁ መስማት አለብህ። ወይስ በንግግርህ ብዛት ጻድቅ የምትሆን ይመስልሃልን? ከሴቶች የሚወለድ ዘመኑ ጥቂት የሆነ ቡሩክ ነው።
3
ንግግር አታብዛ፤ የሚከራከርህ የለምና።
4
አንተ፦ በሥራዬ ንጹሕ ነኝ በፊቱም ጻድቅ ነኝ አትበል።
5
ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት!
6
የጥበቡን ኀይል ቢገልጥልህ! ባንተ ላይ ያለው እጥፍ ነውና። ያንጊዜም ከእግዚአብሔር ዘንድ በበደልህ ያገኘህ ትክክል እንደ ሆነ ታውቃለህ።
7
“የእግዚአብሔርን ፍለጋ ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክ ወደ ፈጠረው ፍጥረት ፍጻሜ ትደርሳለህን?
8
ሰማይ ከፍ ያለ ነው፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ የጠለቁ ነገሮች አሉ፤ ምን ታውቃለህ?
9
ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፥ ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።
10
እርሱ ሁሉን ቢገለብጥ፥ ምን አደረግህ? የሚለው ማን ነው?
11
እርሱ የኃጥኣን ሰዎች ሥራን ያውቃል፤ በደልንም ቢያይ ዝም ብሎ አይመለከትም፤ ይህንም አስተዋይ ሰው ያስተውላል።
12
ነገር ግን በከንቱ ነገርን የሚፈልግ ሰው፥ ከሴትም የሚወለድ ሟች የሜዳ አህያን ይመስላል።
13
አንተ ልብህን ንጹሕ ብታደርግ፥ እጆችህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥
14
በእጆችህ በደል ቢኖር ካንተ አርቀው፤ በልብህም ኀጢአት አይኑር፤
15
በዚያን ጊዜ ፊትህ በንጹሕ ውኃ እንደ ታጠበ ያበራል፥ መተዳደፍህንም ታስወግዳለህ፥ አትፈራምም።
16
መከራህንም እንዳለፈ ማዕበል ትረሳለህ፥ ከእንግዲህም ወዲያ አትደነግጥም።
17
ጸሎትህ እንደ አጥቢያ ኮከብ ይሆናል። ሕይወትህም እንደ ቀትር ብርሃን ያበራል።
18
ተስፋህንም ታገኝ ዘንድ ተዘልለህ ትቀመጣለህ፤ ያለ ኀዘንና ጭንቀትም በደኅንነት ትኖራለህ።
19
ታርፋለህ፥ የሚዋጋህም የለም፤ ብዙ ሰዎችም ይመጣሉ፤ ልመናም ያቀርቡልሃል።
20
የኃጥኣን መድኀኒታቸው ታልቃለች። ተስፋቸውንም ያጣሉ፥ የዝንጉዎች ዐይኖችም ይጠፋሉ።”
← Chapter 10
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 12 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42