bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Job 24
Job 24
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 23
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 25 →
1
“እግዚአብሔር ዘመኖችን ለምን ረሳቸው?
2
ኃጥኣን የድንበሩን ምልክት አለፉ፤ እረኛውንም ከመንጋዎቹ ጋር ይነጥቃሉ።
3
የድሃአደጎቹን አህያ ይነዳሉ የመበለቲቱንም በሬ ስለ መያዣ ይወስዳሉ።
4
ደካሞችን ከእውነት መንገድ ያወጣሉ፤ የምድርም የዋሃን ሁሉ በአንድነት ይሸሸጋሉ።
5
እነሆ፥ በምድረ በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች ሆኑ። ስለ እኔም ሥራቸውን ትተው ይወጣሉ፤ መብል፦ ከልጅነታቸው ጀምሮ ይጥማቸዋል።
6
“የራሳቸው ያልሆነውን እርሻ ያለ ሰዓቱ ያጭዳሉ። ኃጥኣን ድሆችን በወይናቸው ቦታ ያለ ዋጋና ያለ ቀለብ ያሠሩአቸዋል።
7
ብዙዎችን የተራቈቱትንም ያለ ልብስ ያሳድሩአቸዋል። መጐናጸፊያቸውንም ይገፍፏቸዋል።
8
በካፊያና ከተራሮች በሚወርድ ጠል ይረጥባሉ፤ መጠጊያም የላቸውምና ቋጥኙን ተተገኑ።
9
ድሃአደጉን ልጅ ከጡቱ ይነጥላሉ፤ ችግረኛውንም ያሠቃያሉ።
10
ችግረኞችን በደሉአቸው፥ ጣሉአቸውም፤ ከተራቡትም የሚጐርሱትን ነጠቋቸው።
11
በጠባብ ቦታ በዐመፅ ይሸምቃሉ፥ የጽድቅንም መንገድ አያውቁም።
12
ድሆችን ከከተማውና ከገዛ ቤቶቻቸው አባረሩአቸው የሕፃናትንም ነፍስ እጅግ አስጮሁ፤
13
“እግዚአብሔር ግን እነዚህን ለምን አልገሠጻቸውም? በምድር ላይ ሳሉ አላስተዋሉም፥ የቅንነት መንገድንም አላዩም። በአደባባይዋም አልሄዱም።
14
ሥራቸውንም ዐውቆ ለጨለማ ዳረጋቸው። በሌሊትም እንደ ሌባ ናቸው።
15
የአመንዝራም ዐይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል፦ የማንም ዐይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል።
16
በጨለማ ቤቶችን ይነድላል፤ በቀን ይሸሸጋሉ፤ ብርሃንንም አያዩም።
17
የጥዋት ብርሃን ለእነርሱ ሁሉ እንደ ሞት ጥላ ነው፤ የሚሆነውን ድንጋጤ ያውቃሉና። ሞትንም ይጠራጠራሉና።
18
እርሱ በውኃ ፊት ላይ በርሮ ያልፋል፤ እድል ፋንታውም በምድር ላይ የተረገመች ናት፤
19
ተክላቸው በምድር ላይ ሲደርቅ ያያሉ። ያላቸውም ድሀኣደጉን በዘበዙት።
20
ከዚህም በኋላ ኀጢአቱን ያስባል። እንደ ጤዛ ትነት ይጠፋል። እንደ ሥራውም ይከፈለዋል። ዐመፀኛም ሁሉ እንደ በሰበሰ ዛፍ ይሰበራል።
21
ለማትወልደው ለመካኒቱ በጎነትን አላደረገላትም፤ ለምትወልደውም አልራራም።
22
ነገር ግን ረዳት የሌላቸውን በቍጣው አጠፋቸው። እርሱም በተነሣ ጊዜ ሰው በሕይወቱ አይታመንም።
23
በታመመም ጊዜ መዳንን ተስፋ አያደርግም። ነገር ግን እርሱ በሕማሙ ይሞታል።
24
ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙዎችን አስጨነቃቸው። እንደ አመድማዶ በሙቀት ይጠወልጋል። ከቃርሚያው እንደሚወድቅ እሸትም ይቈረጣል።
25
እንዲህስ ባይሆን ሐሰተኛ ነህ የሚለኝ፥ ነገሬንስ እንደ ኢምንት የሚያደርገው ማን ነው?”
← Chapter 23
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 25 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42