bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Job 32
Job 32
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 31
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 33 →
1
ኢዮብም በፊታቸው ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና እነዚያ ሦስቱ ወዳጆቹ ለኢዮብ ለመመለስ ዝም አሉ።
2
ከአውስጢድ ሀገር ከአራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊዩስ ተቈጣ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።
3
ደግሞም እንደ ኀጢአተኛ አደረጉት እንጂ ለኢዮብ የሚገባ መልስ መመለስ ስላልቻሉ በሦስቱ ባልንጀሮቹ ላይ ተቈጣ።
4
ኤሊዩስ ግን ከእርሱ ይልቅ ሽማግሌዎች ነበሩና ለኢዮብ መልስ ለመስጠት ጠብቆ ነበር።
5
ኤሊዩስም በእነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ባየ ጊዜ በቍጣው ተቈጣቸው።
6
የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤልዩስም መለሰ፥ እንዲህም አለ፥ “እኔ በዕድሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ዕውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ።
7
እንደዚህም አልሁ፥ “የሚናገሩ ዓመታት አይደሉም፥ በዓመታት ብዛት ሰዎች ጥበብን አያውቋትም።
8
ነገር ግን በሟች ሰው ውስጥ መንፈስ አለ፥ ሁሉን የሚችል የእግዚአብሔር መንፈስም ያስተምራል።
9
በዕድሜ ያረጁ ጠቢባን አይደሉም፥ ሽማግሌዎችም ፍርድን አያስተውሉም።
10
ነገር ግን፦ ስሙኝ፤ እኔ ደግሞ የማውቀውን እገልጥላችኋለሁ አልሁ።
11
እነሆ፥ ንግግሬን አድምጡኝ፤ የምትናገሩትን ነገር እስክትመረምሩ ድረስ እየሰማችሁት እነግራችኋለሁ።
12
እንዲሁም ልብ አደረግሁ፤ እነሆም፥ ከእናንተ መካከል ኢዮብን የገሠጸ፥ ወይም ለተናገረው ቃልን የመለሰ የለም።
13
እናንተም፦ ከእግዚአብሔር ጥበብን አግኝተናል፤ አብዝተናልም እንዳትሉ ተጠንቀቁ።
14
እናንተ ግን እንዲህ ያለ ነገር እንዲናገር ለሰው መብት ሰጣችሁት።
15
“እናንተ ፈራችሁ፥ ዳግመኛም አልመለሳችሁም፤ ከአፋችሁም ቁም ነገር ጠፋ።
16
እኔ በትዕግሥት ጠበቅሁ እንጂ አልተናገርሁም። እናንተ ዝም ብላችሁ ቆማችሁ፥ አልመለሳችሁምና።”
17
ኤልዩስም መለሰ፥ እንዲህም አለ፦ “ደግሜ እናገራለሁ።
18
እኔ ቃል ተሞልቻለሁና፥ በውስጤም ያለ መንፈስ አስጨንቆኛልና።
19
በተሃ ጠጅ እንደ ተሞላና ሊቀደድ እንደ ቀረበ አቁማዳ፥ ወይም እንደ አንጥረኛ ወናፍ እነሆ፥ አንጀቴ ሆነ።
20
ጥቂት እንድተነፍስ እናገራለሁ። ከንፈሬንም ገልጬ እመልሳለሁ።
21
ከሰው የተነሣ አላፍርምና፥ ከሟች ሰውም የተነሣ አላፈገፍግምና።
22
ለሰው ፊት ማድላትን አላውቅም፤ ከሰውም የተነሣ የማፍረው ካለ ትሎች ይብሉኝ።
← Chapter 31
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 33 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42