bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Job 7
Job 7
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 6
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 8 →
1
“ጥንቱን በምድር ላይ የሰው ሕይወት ጥላ አይደለምን? ኑሮውስ እንደ ቀን ምንደኛ አይደለምን?
2
ወይም ጌታውን እንደሚፈራ አገልጋይ ጥላውንም እንደሚመኝ፥ ወይም ደመወዙን እንደሚጠብቅ ምንደኛ አይደለምን?
3
እንዲሁ እኔ የከንቱ ወራትን ታገሥሁ፥ የፃዕርም ሌሊት ተወሰነችልኝ።
4
በተኛሁም ጊዜ፦ መቼ ይነጋል? እላለሁ፤ በተነሣሁም ጊዜ ዳግመኛ መቼ ይመሻል? እላለሁ፤ ከማታ እስከ ጥዋት ድረስ መከራን ጠገብሁ።
5
ሥጋዬ በትልና በመግል በስብሶአል፥ ቍስሌን በገል እያከክሁ አለቅሁ። ዐመድም ሆንሁ።
6
ሕይወቴ እንደ ሸማኔ መወርወርያ፥ ቀላል ሆነች በከንቱ ተስፋም ጠፋሁ።
7
ሕይወቴ እስትንፋስ እንደ ሆነች አስብ፤ ዐይኔም መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ ዳግመኛ አታይም።
8
የሚያየኝ ሰው ዐይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፤ ዐይንህ በእኔ ላይ ይሆናል፤ እኔም አልገኝም።
9
ደመና ከሰማይ ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ ወደ መቃብር የሚወርድ ሰው ዳግመኛ አይወጣም።
10
ወደ ቤቱም ዳግመኛ አይመለስም፥ ስፍራውም ዳግመኛ እርሱን አያውቀውም።
11
ስለዚህም እኔ አፌን አልከለክልም፤ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፤ የነፍሴንም ምሬት በኀዘን እገልጣለሁ።
12
ጠባቂ አዝዘህብኛልና፥ እኔ ባሕር ወይስ አንበሪ ነኝን?
13
እኔም፦ አልጋዬ ያጽናናኝ ይሆን? መኝታዬስ ደስ ያሰኘኝ ይሆን? እላለሁ።
14
አንተም በሕልም ታስፈራራኛለህ፥ በራእይም ታስደነግጠኛለህ፤
15
ሕይወትን ከመንፈሴ ትለያለህ። አጥንቶቼንም ከሞት ትጠብቃለህ።
16
እንድታገሥ ለዘለዓለም እኖራለሁን? ሕይወቴ ከንቱ ነውና ከእኔ ራቅ።
17
ሰው ምንድን ነው? ከፍ ከፍ ታደርገው ዘንድ፥ ልቡናውንም ትጐበኘው ዘንድ፥
18
ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥ በዕረፍቱም ትፈርድለት ዘንድ፥
19
የማታሳርፈኝ እስከ መቼ ነው? ምራቄንስ እስክውጥ ድረስ የማትለቅቀኝ እስከ መቼ ነው?
20
የሰውን ልብ፦ የምታውቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ እንግዲህ ምን ላደርግልህ እችላለሁ? ስለምን እኔን ለመከራ አደረግኸኝ? ስለ ምን በአንተ ላይ እንድናገር በአምሳልህ ፈጠርኸኝ? ስለ ምንስ እኔ ሸክም ሆንሁብህ?
21
ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ስለ ምን አታነጻም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በማለዳም አልነቃም።”
← Chapter 6
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 8 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42