bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Job 5
Job 5
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 4
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 6 →
1
“አሁንም የሚመልስልህ ካለ ጥራ፥ ከቅዱሳን መላእክትም የምታየው ካለ?
2
ሰነፉን ሰው ቍጣ ይገድለዋልና፥ ቅንዓትም ሰነፉን ያጠፋዋል።
3
ሰነፎችን ሥር ሰድደው አየኋቸው፥ በድንገትም መኖሪያቸው ጠፋች።
4
ልጆቻቸው ከደኅንነት ርቀዋል፥ በበርም ውስጥ ይቀጠቅጡአቸዋል፤ መከራም ያጸኑባቸዋል፥ የሚታደጋቸውም የለም።
5
እነርሱ የሰበሰቡትንም ጻድቃን ይበሉታል። እነርሱን ግን ክፋት ቷጋቸዋለች፥ ኀይላቸውም ይደክማል።
6
ችግር ከምድር አይወጣምና፥ መከራም ከተራሮች አይበቅልምና፤
7
የአሞራ ግልገሎች ግን ወደ ላይ እየበረሩ ከፍ እንዲሉ፥ ሰው እንዲሁ ለድካም ተወልዶአል።
8
“እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምነው ነበር፥ የሁሉ ጌታ እግዚአብሔርንም እጠራው ነበር።
9
እርሱ የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን የከበረና ድንቅ ነገር ያደርጋል።
10
በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ ከሰማይም በታች ውኃን ይልካል።
11
የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋቸዋል፥ የወደቁትንም ያነሣቸዋል።
12
የተንኰለኞችን ምክር ይለውጣል፥ እጆቻቸውም ቅን አይሠሩም።
13
ጠቢባንንም በተንኰላቸው ይይዛቸዋል፤ ምክርን የሚጐነጉኑ ሰዎችን አሳብ ያጠፋል።
14
በቀን ጨለማ ያገኛቸዋል፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ።
15
በጦርነት ይጠፋሉ፤ ደካማውም ከኀያሉ እጅ ያመልጣል።
16
ለምስኪኑ ተስፋ አለውና፤ የዐመጸኛም አፍ ይዘጋልና።
17
“ነገር ግን እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ።
18
እርሱ ይሰብራል፥ ዳግመኛም ይጠግናል፤ ይቀሥፋል፥ እጆቹም ይፈውሳሉ።
19
ስድስት ጊዜ ከክፉ ነገር ያድንሃል፥ በሰባተኛውም ጊዜ ክፋት አትነካህም።
20
በራብ ጊዜ ከሞት ያድንሃል፥ በጦርነትም ጊዜ ከሰይፍ እጅ ያድንሃል።
21
ከምላስ ጅራፍ ይሰውርሃል፥ ከምትመጣብህም ክፋት አትፈራም።
22
በኃጥኣንና በዐመጸኞች ላይ ትስቅባቸዋለህ፤ ከምድረ በዳ አራዊትም አትፈራም፤
23
የምድረ በዳ አራዊትም ከአንተ ጋር ይስማማሉ።
24
ያንጊዜ ቤትህ በሰላም እንዲሆን ታውቃለህ፤ ከንብረትህም አንዳች አይጐድልም።
25
ዘርህም ብዙ እንዲሆን፥ ልጆችህም እንደ አማረ መስክ ሣር እንዲሆኑ ታውቃለህ።
26
በወራቱ የደረሰ አዝመራ እንዲሰበሰብ፥ የእህሉ ነዶም በወቅቱ ወደ አውድማ እንዲገባ፥ በረዥም ዕድሜ ወደ መቃብር ትገባለህ።
27
እነሆ፥ ይህን ዐውቀን መረመርን፥ የሰማነውም ይህ ነው፤ አንተ ግን አንዳች ሠርተህ እንደ ሆነ ለራስህ ዕወቅ።”
← Chapter 4
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 6 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42