bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Job 28
Job 28
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 27
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 29 →
1
“በእውነቱ ብር የሚወጣበት ቦታ አለ፥ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።
2
ብረትም ከመሬት ውስጥ ይወጣል፤ መዳብም እንደ ድንጋይ ይፈለጣል።
3
ለጨለማ ወሰንን ያደርጋል፤ እርሱ ሁሉን ይመረምራል፥ የጨለማንና የሞት ጥላ ድንጋይንም ይመረምራል።
4
በአፈር ምክንያት እንደሚከፈል ወንዝ የጽድቅን መንገድ የረሱ በኀጢአታቸው ይደክማሉ። ከሰዎችም መካከል ይለያሉ።
5
እንጀራ ከምድር ውስጥ ይወጣል፤ በእሳትም እንደሚሆን ታችኛው ይገለበጣል።
6
ድንጋይዋ እንደ ሰንፔር፥ ወርቅዋም እንደ አፈር የሆነ መሬት አለች።
7
መንገድዋን ዎፍ አያውቀውም፥ የንስርም ዐይን አላየውም።
8
የትዕቢተኞች ልጆች አልረገጡአትም፥ ደቦል አንበሳም በውስጥዋ አላለፈባትም።
9
ሰው ወደ ቡላድ ድንጋይ እጁን ይዘረጋል፥ ተራራዎችንም ከመሠረታቸው ይገለብጣቸዋል።
10
ከድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያ ይወቅራል፤ ዐይኔም የከበረውን ነገር ሁሉ ታያለች።
11
የፈሳሹንም ጥልቀት ይገልጣል። ኀይሉንም በብርሃን ይገልጣል።
12
“ነገር ግን ጥበብ ወዴት ትገኛለች? የጥበብስ ሀገርዋ ወዴት ነው?
13
ሟች ሰው መንገድዋን አያውቅም፤ በሰዎችም ዘንድ አትገኝም።
14
ቀላይ፦ በእኔ ውስጥ የለችም ትላለች። ባሕርም፦ በእኔ ዘንድ የለችም ይላል።
15
ስለ እርስዋም ማንም ምዝምዝ ወርቅ አይሰጥም ብርም በእርስዋ ለውጥ አይመዘንም።
16
ከአፌር ወርቅም ጋር አትወዳደርም። በከበረ መረግድና በሰንፔር አትገመትም።
17
ወርቅና ብርጭቆ አይወዳደሩአትም፥ የወርቅም ጥሬ ዕቃ የእርስዋ ለውጥ አይሆንም።
18
ዛጎልና አልማዝ አይታሰቡም። አንተ ግን እጅግ ከከበሩ ነገሮች ሁሉ ይልቅ ጥበብን አቅርባት።
19
የኢትዮጵያ ሉል አይተካከላትም፥ በጥሩም ወርቅ አትገመትም።
20
“እንግዲያ ጥበብ ከወዴት ትገኛለች? የማስተዋልስ ሀገሯ ወዴት ነው?
21
በሰው ሁሉ ዘንድ ተረስታለች፥ ከሰማይ ወፎችም ተሰውራለች።
22
ሞትና ሲኦል ወሬዋን በጆሮቻችን ሰማን ብለዋል።
23
“እግዚአብሔር መንገድዋን አሳመረ፥ እርሱም ስፍራዋን ያውቃል።
24
እርሱም በሰማይ ያለውን ይመለከታል፥ በምድርም ያለውን ሁሉ ያውቃል።
25
ለነፋስ ሚዛንን ለውሆችም መስፈሪያን አደረገ።
26
እነዚህን በፈጠረ ጊዜ እንዲሁ ዐውቆ ቈጠራቸው። ለዝናም ሥርዐትን ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን አደረገ።
27
በዚያን ጊዜ አያት፥ ገለጣትም፤ አዘጋጃትም፥ አከበራት፥ ደግሞም መረመራት።
28
ሰውንም፦ ‘እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራቅም ማስተዋል ነው’ ” አለው።
← Chapter 27
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 29 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42