bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Job 30
Job 30
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 29
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 31 →
1
“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ ለመዘባበት በእኔ ላይ ሳቁ፤ አባቶቻቸውን የናቅሁባቸውና እንደ መንጋዬ ውሾች ያልቈጠርኋቸው ዛሬ ለብቻቸው ይገሥጹኛል።
2
የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምንድን ነው? ሞት በላያቸው ይምጣ።
3
ትላንት በድካምና በውርደት ከምድረ በዳ ያመለጡ፥ ከረኃብ የተነሣ ተሰድደው ይለምናሉ።
4
እየዞሩ የሚለምኑና የሚበሉ በቅልውጥም የሚኖሩ ወራዶች፥ ዐመፀኞችና ከበጎ ነገሮች ሁሉ የተቸገሩ ናቸው። ከታላቅ ረኃብም የተነሣ ጨው ጨው የሚለውን የእንጨት ሥር ይበላሉ።
5
“ሌቦች በእኔ ላይ ተነሡ፥
6
በሸለቆው ፈረፈርና በምድር ጕድጓድ ውስጥ በዓለትም ዋሻ ውስጥ ይኖራሉ፤
7
በገደል ማሚቶው መካከል ይጮኻሉ፤ በሳማ ውስጥም ይሸሸጋሉ።
8
የሰነፎችና የክፉዎች ሰዎች ልጆች ናቸው፤ ስማቸውና ክብራቸው ከምድር የጠፋ ነው።
9
አሁንም እኔ መዝፈኛና መተረቻ ሆንኋቸው።
10
ተጸየፉኝ፥ ከእኔም ራቁ፤ ምራቃቸውንም በፊቴ መትፋትን አልታከቱም።
11
የቀስቱን አፎት ከፍቶ ክፉ አደረገብኝ፤ በፊቴም ልጓሙን ሰደደ።
12
በኀይሉ ቀኝ ተነሣብኝ፤ እግሮቹንም ዘረጋብኝ፤ የሞትንም መንገድ በእኔ ላይ አደረገ።
13
ፍለጋዬን አጠፋ፤ ልብሴን ገፈፈኝ፥ በቀስቱም ነደፈኝ።
14
እንደ ወደደ አደረገብኝ፤ በመከራም እዛብራለሁ።
15
ድንጋጤ በላዬ ተመላለሰችብኝ፥ ነፍሴ ከእኔ ላይ እለይ እለይ አለች፥ ደኅንነቴም እንደ ተበተነ ደመና አለፈች።
16
“አሁንም ነፍሴ በውስጤ ፈሰሰች፤ ጭንቀትም በእኔ ላይ ሞላ፤
17
በሌሊት ሁሉ አጥንቶች በደዌ ይነድዳሉ፥ ጅማቶችም ይቀልጣሉ።
18
ከታላቁ ደዌ ኀይል የተነሣ ልብሴ ተበላሸች፤ የልብሴ ክሳድ አነቀችኝ፥ ቀሚሴም በአንገቴ ተጣበቀ።
19
እርሱ እንደ ጭቃ ረገጠኝ፥ ዕድል ፋንታዬም አፈርና አመድ ሆነ።
20
ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልሰማኸኝምም፤ እነርሱ ግን ቆመው ተመለከቱኝ።
21
ምሕረት የሌላቸው ሰዎች ደበደቡኝ፥ የገረፈችኝ እጅም በረታች።
22
በኀዘን አኖርኸኝ፥ ከሕይወቴም አራቅኸኝ።
23
ሞት እንደሚያጠፋኝ አውቃለሁና ለሟችም ሁሉ ማደሪያው ምድር ናትና።
24
እኔ ራሴ ልታነቅ በወደድሁ ነበር ይህም ባይሆን ሌላው እንዲሁ እንዲያደርግልኝ እለምናለሁ።
25
ረዳት ለሌለው ሰው አለቀስሁ የተቸገረ ሰውን ባየሁ ጊዜ ጮኽሁ።
26
ነገር ግን በጎ ነገርን በተጠባበቅኋት ጊዜ እነሆ ክፉ ቀኖች መጡብኝ፤ ብርሃንን ተስፋ አደረግሁ፥ ጨለማም መጣብኝ።
27
ሆዴ ፈላች፥ አላረፈችምም፤ የችግርም ዘመን መጣችብኝ።
28
በጠባቡ ሄድሁ፥ የሚያሰፋልኝም አጣሁ፥ በጉባኤም መካከል ቆሜ እጮኻለሁ።
29
ለሌሊት ዎፍ ወንድም፥ ለሰጎንም ባልንጀራ ሆንሁ።
30
ቍርበቴ እጅግ ጠቈረ፥ አጥንቶቼም ከትኩሳት የተነሣ ተቃጠሉ።
31
ስለዚህ ሕማሜ መሰንቆ፥ ልቅሶዬም በገና ሆነብኝ።
← Chapter 29
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 31 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42