bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Job 12
Job 12
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
← Chapter 11
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 13 →
1
ኢዮብም መለሰ፥ እንዲህም አለ፦
2
“በእርግጥ እናንተ ዓይነተኞች ሰዎች ናችሁ፤ ጥበብም በእናንተ ዘንድ ትፈጸማለች።
3
ነገር ግን እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ልብ አለኝ። እኔ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም፥ እንደዚህ ያለውን ነገር የሚያውቅ ማነው?
4
እግዚአብሔርን የጠራሁ እርሱም የመለሰልኝ እኔ፥ ለባልንጀራው መሣለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፤ ጻድቁና ንጹሑ ሰው መሣለቂያ ሆኖአል።
5
እርሱ በተወሰነው ዕድሜ በሌሎች እንዲወድቅ፥ ቤቱም በኃጥኣን እንዲፈርስ ተዘጋጅቶአል። ነገር ግን ማንም ክፉ ሆኖ ንጹሕ እንደሚሆን አይመን።
6
እግዚአብሔርን የሚያስቈጡትን ሰዎች፥ እርሱ የሚመረምራቸው አይደለምን?
7
“አሁን ግን እንስሶችን ጠይቅ፥ ያስተምሩህማል፤ የሰማይንም ወፎች ጠይቅ፥ ይነግሩህማል።
8
ለምድር ንገራት፥ እርስዋም ትተረጕምልሃለች፤ የባሕርም ዓሣዎች ያስረዱሃል።
9
የእግዚአብሔር እጅ ይህን ሁሉ እንዳደረገ ከእነዚህ ሁሉ የማያውቅ ማን ነው?
10
የሕያዋን ሁሉ ነፍስ፥ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናትና።
11
ዦሮ ነገርን የሚለይ አይደለምን? ጕረሮስ መብልን የሚቀምስ አይደለምን?
12
በረዥም ዘመን ጥበብ፥ በመኖር ብዛትም ዕውቀት ይገኛል።
13
በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኀይል አለ፤ ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው።
14
እነሆ፥ እርሱ ቢያፈርስ፥ ማን ይሠራል? በሰውም ላይ ቢዘጋበት ማን ይከፍታል?
15
እነሆ፥ ዝናብን ከሰማይ ቢከለክል ምድርን ያደርቃታል፤ እንደገና ቢተዋትም ትጠፋለች፤ ትገለበጣለችም።
16
ኀይልና ብርታት በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ ዕውቀትና ማስተዋልም ለእርሱ ናቸው።
17
መካሮችንም እንዲማረኩ ያደርጋቸዋል፤ የምድር ፈራጆችንም አላዋቆች ያደርጋቸዋል።
18
ነገሥታትንም በዙፋን ያስቀምጣቸዋል፤ ወገባቸውንም በኀይል መታጠቂያ ያስታጥቃቸዋል።
19
ካህናተ ጣዖትን እንዲማረኩ ያደርጋቸዋል፤ የምድር ኀያላንንም ይገለብጣቸዋል።
20
ከታመኑ ሰዎችም ቋንቋን ይለውጣል፤ የሽማግሌዎችንም ምክር ያውቃል።
21
በአለቆች ላይ ውርደትን ያመጣል፥ ትሑታንንም ያድናቸዋል።
22
ጥልቅ ነገርን ከጨለማ ይገልጣል፤ የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።
23
አሕዛብን ያቅበዘብዛቸዋል፤ ያጠፋቸዋልም፤ አሕዛብንም ይገለብጣቸዋል፤ ያፈልሳቸዋልም።
24
የምድር አለቆች ማስተዋልን ይለውጣል። በማያውቁት መንገድም ያቅበዘብዛቸዋል።
25
ብርሃንም ሳይኖር በጨለማ ይርመሰመሳሉ፤ እንደ ሰካራምም ይፍገመገማሉ።
← Chapter 11
Jump to:
Chapter 1
Chapter 2
Chapter 3
Chapter 4
Chapter 5
Chapter 6
Chapter 7
Chapter 8
Chapter 9
Chapter 10
Chapter 11
Chapter 12
Chapter 13
Chapter 14
Chapter 15
Chapter 16
Chapter 17
Chapter 18
Chapter 19
Chapter 20
Chapter 21
Chapter 22
Chapter 23
Chapter 24
Chapter 25
Chapter 26
Chapter 27
Chapter 28
Chapter 29
Chapter 30
Chapter 31
Chapter 32
Chapter 33
Chapter 34
Chapter 35
Chapter 36
Chapter 37
Chapter 38
Chapter 39
Chapter 40
Chapter 41
Chapter 42
Chapter 13 →
All chapters:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42